ምርጫ ቦርድ የቀድሞ አርማውን ከነጠባሳው ቀርፎ ጣለ፣ አዲሱን ዓርማ ይፋ አደረገ

Views: 133

ጌታቸው ወርቁ

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ እያከናወነ ያለውን የምርጫ ሥርዓት ማሻሻያ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ  ለባለድርሻ አካላት ገለጸ።

 

ዛሬ ዓርብ የካቲት 6 ቀን 2012 ዓም በአዲስ አበባ በኢትዮጵያ አየርመንገድ ስካይላይት ሆቴል እየተከናወነ ባለው የምርጫ ባለድርሻ አካላት ኮንፍረንስ ላይ ምርጫ ቦርድ አዲሱን ዓርማው ይፋ አድርጓል።

 

የምርጫ ባለድርሻ አካላት ኮንፈረንሱን የከፈቱት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ፣ ይህ ኮንፍረንስ የማሻሻያ ሂደቱ ትክክለኛነትን ጠብቆ እየሄደ መሆኑን አውቃችሁ ሀገራዊ የፀጥታ ችግሮችን ለማስወገድ ባለድርሻ አካላት ሁሉ የበኩላቸውን እንዲወጡና የፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት ተንቀሳቅሰው ፕሮግራሞቻቸውን ለህዝብ እንዲያስታውቁ ዓውዱ እንዱሰፋ እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

 

ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የሚጠበቁ ሚናዎች አሉ ያሉት የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን፣ አንደኛው ሚናችሁ የሆነውን ከሰለጠነ የፖለቲካ ፓርቲ የሚጠበቅባችሁን ሁሉ እንድትወጡ አሳስባለሁ ብለዋል።

 

የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አባላቶቻቸው መድረኩን በነፃነት ተጠቅመው ሃሳባቸውን እንዲያንሸረሽሩም ጋብዘዋል።

 

በዚህ ለሙሉ ቀን በሚከናወነው የምርጫ ቦርድ ሁለተኛ ኮንፈረንስ ላይ፣ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ሥራዎች እንቅስቃሴውን ለባለድርሻ አካላት መረጃ የሚያካፍልበት፣ የ2012 የተከለሰ አጠቃላይ የምርጫ ሰሌዳ ይፋ የሚያደርግበት እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ስለመተባበር ግዴታዎች ሚና እና ሃላፊነት ውይይት ማካሄድና የእነርሱን ግብረመልስ ማድመጥ ይሆናል ተብሏል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com