እስጢፋኖስ አካባቢ የመኪና አደጋ ደረሰ

Views: 246

በአዲስ አበባ ከተማ እስጢፋኖስ አካባቢ የሲሚንቶ ማቡኪያ ማሽን (ሚክሰር) ያለው ከባድ ተሽከርካሪ ፍሬን በጥሶ አደጋ አደረሰ፡፡

አደጋው የደረሰው ትላንት የካቲት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ተሽከርካሪው ፍሬን በጥሶ የባቡር የእግረኛ መሻገሪያ ደረጃ ስር በመግባቱ ነው ተብሏል፡፡

በተከሰተው አደጋ አንድ የታክሲ ሹፌር ጉዳት ደርሶበት ወደ ሆስፒታል የሄደ ሲሆን፤ የሰው ህይወት እንዳልጠፋ ግን ለማወቅ ተችሏል ሲል የዘገበው አዲስ ማለዳ ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com