በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የነበረው ድርድር መቋጫ አልተገኘለትም

Views: 217

በኢትዮጵያ፣በሱዳን እና በግብጽ መካከል በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውኃ አሞላል እና አለቃቀቅን በተመለከተ የረቂቅ የስምምነት ሰነድ ለመፈረም ሲያካሂዱት የነበረው ድርድር መቋጫውን ሳያገኝ ተጠናቅቋል፡፡

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው እንዳስታወቁት፣ በአገራቱ መካከል ላለፉት ሁለት ቀናት በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በግድቡ የውኃ አሞላል እና አለቃቀቅን በተመለከተ ሲያካሄዱት የነበረው ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ዝግጅት ከድምዳሜ ላይ መድረስ ሳይችሉ ቀርተዋል ብለዋል፡፡

የኢፌዴሪ የውኃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር ኢ/ር) በዚህ ሳምንት የሦስቱ አገራት የሕግ ባለሞያዎች የደረሱበትን ረቂቅ ስምምነት ዝግጅት በኢትዮጵያ በኩል ለመገምገም ወደ ስፍራው ማቅናታቸውም የሚታወስ ነው፡፡

አሜሪካ እና ዓለም ባንክ በተገኙበት ተከታታይ ምክክር እና ድርድር ሦስቱ አገራት ከስምምነት ደርሰው በዚህ ወር ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡

ሦስቱ አገራት በግድቡ ዙሪያ የጀመሩት ንግግር መቼ መቋጫውን እንደሚያገኝ የታወቀ ነገር የለም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር የስምምነት ሂደቱ በጋራ መክረን የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስጠበቅ እና የጠራ አቋም ለመያዝ እንዲዘገይ እንዳዘዙ መናገራቸውም ይታወቃል ሲል የዘገበው ኢቲቪ ነው፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com