በጎ ተፅዕኖ እያሳደሩ ላሉ የኪነጥበብ ሰዎች የእራት ግብዣ ተዘጋጀ

Views: 193

ቅን ኢትዮጵያ በማህበረሰባችን ውስጥ በጎ ተፅዕኖ እያሳደሩ ላሉ የኪነጥበብ ሰዎች’ ‹‹ኪነጥበብና ቅንነት›› በሚል ርዕስ  ዛሬ ሃሙስ የካቲት 5 ቀን 2012 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ከ 11: 30 ጀምሮ የእራት ግብዣ አዘጋጅቷል።

ቅን ኢትዮጵያ ማህበር ከተቋቋመ 10 ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን፣ በዶክተሮች፣ ፕሮፌሰሮች እና በትውልድ አሳቢዎች የተመሠረተ ማህበር እንደሆነ ይታወቃል።

በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በጎ አሳቢነት፣ መደናነቅን እና መከባበርን የሚሰብኩ ዝግጅቶች ከተለያዩ ከሚመለከታቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር መሰል ዝግጅቶችን ማቅረቡ ይታወሳል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com