በ6 ወር 127.5 ቢሊዮን ብር ተሰበሰበ

Views: 171

ገቢዎች ሚንስትር፣ በ2012 ዓ.ም የመጀመሪያውን ስድስት ወራት የገቢ አሰባሰብ የዕቅዱን መቶ-ከመቶ ማሳካቱን አስታወቀ፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት የግብር አሰባሰብ ከፍተኛ የአፈፃጸመ ጉድለት የነበረበት ወቅት መሆኑ በገቢዎች ሚንስትር ተገልጿል፡፡

በገቢዎች ሚንስትር በስትራቴጂ አጋርነት ሥራ አመራር ዳይሮክቴሬት- ዳይሬክተር አቶ ከበደ ልደቱ እንደገለጹት፣ በ2012 ዓ.ም መጀመሪያ ስድስት ወራት የገቢ አሰባሰብ መርሃ-ግብር፣ 125 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ፣ 127 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር (ከዕቅዱ 101 በመቶ) ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡

ይህም፣ ከባለፈው ዓመት አንፃር የ28 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር (ከዕቅዱ 29 በመቶ) እድገት አሳይቷል ብለዋል፡፡

በአንፃሩ፣ የ2012 ዓ.ም የስድስት ወራት የንግድ ትርፍ የሕግ ተገዢነት ላይ፤ ኪሳራ በማሳወቅ ሂደት ላይ፣ የውሸት ኪሳራ ማስመዝገብ ለተቋሙ የሕግ ፈተና ሆኗል በማለት ገልጸዋል፡፡

የገቢዎች ሚንስትር ዛሬ ሐሙስ የካቲት 05 ቀን 2012 ዓ.ም በአየርመንገድ ስካይ ላይት ሆቴል ‹‹የታክስ ሕግ ተገዢነት እና የሴት ግብር ከፋዮች ሚና›› በሚል መሪ ቃል ነጋዴ ሴቶችን ሰብስቦ በአወያየበት መድረክ፣ ከነጋዴ ሴቶች በተጨማሪ፣ የድርጅትና የተቋማት ሴት ኃላፊዎች፣ የሂሳብ ባለሟሎችና የሚንስትር መሥሪያ ቤቱ ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com