ጌትነት እንየው በመድረክ ሊከብር ነው

Views: 238

የከያኒ ጌትነት እንየው የመሐፍ ምረቃና የምስጋና ፕሮግራም የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲካሄድ መርሃ ግብር ተያዘለት።

እውቁ የቴአትር ባለሙያና ገጣሚ ጌትነት እንየው ማክሰኞ  ሊካሄድ የነበረው ”ውበትን ፍለጋ”  መፅሐፍ ምረቃና የምስጋና ፕሮግራም የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ታውቋል።

በፕሮግራሙ ላይ በአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ የቴአትርና ኪነጥበባት ትምህርት ክፍል መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ ወርቁ፣ አርቲስቶቹ ደበበ እሸቱ፣ አበበ ባልቻ፣ ዓለማየሁ ታደሰ እንዲሁም ገጣሚያንም ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።

በዕለቱም ከያኒው ለረጅም ዓመታት ላበረከተው የኪነጥበብ አበርክቶ ምስጋና የሚቀርብበት ሲሆን፣ እውቁን ተውኔቱን ‹‹ውበትን ፍለጋ››ን ጨምሮ፣ በርካታ ስራዎችን የያዘው መጽሐፉ የሚመረቅ ሲሆን፤ ዘጋቢ ፊልም፣ ቅንጭብ ተውኔትና ሙዚቃም ለታዳሚ እንደሚቀርብ ተገልጿል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com