‹‹በጨቅላ ህጻናትና እናቶች ሞት ቅነሳ ረገድ የተሰራው ሥራ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት ነው››

Views: 275

ሜሊንዳና ጌትስ ፋውንዴሽን

የሜሊንዳና ጌትስ ፋውንዴሽን የ2020 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫውን ለህዝብ ይፋ አደረገ፡፡ በድህነት ቅነሳና በጤና አጠባበቅ ጉዳዮች በዓለም ዙሪያ የተሰሩ ሥራዎችንም ዳሷል፡፡

የሜሊንዳና ጌትስ ፋውንዴሽን ‹‹ከባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውጤት ተነስተን አስደናቂ ውጤት ማስመዝገብ እንችላለን›› የሚል ርዕስ በተሰጠው መግለጫው፣ የፋውንዴሽኑ የሁለት አስርት ዓመታት በተለይ በጤናና ትምህርት ዙሪያ ያሉ ስጋቶችን ለመቀነስ የተሰሩ ሥራዎችን ለመተንተን ሞክሯል፡፡

ኢትዮጵያ በተለይ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በርካታ ስኬቶችን እያስመዘገበች ያለች ሃገር ናት፤ ዜጎቿን ከድህነት ለማውጣት በምታደርገው ጥረት አስደናቂ ቁጥሮችን ማስመዝገብም የቻለች ሀገር ናት ሲል ገልጿታል፡፡

አ.ኤ.አ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በሃገሪቱ ድህነት በ46 በመቶ ቀንሷል የሚለው ሜሊንዳና ጌትስ ፋውንዴሽን፣ በጨቅላ ህጻናትና እናቶች ሞት ቅነሳ ረገድ የተሰራው ሥራ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት ነው ብሏል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ሞት ከ1000 ህጻናት ወደ 191፤ የሚወለዱ ህጻናት ደግሞ ወደ 5.7 በመቶ ቀንሷል፤ በወሊድ ጊዜ የሚሞቱ እናቶች ቁጥር ደግሞ ከ100,000 እናቶች ወደ 191 አሽቆልቁሏል ሲል ሃተታውን አቅርቧል፡፡

ከ1990 ዓ.ም. ጀምሮ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት በሚመጣ የህጻናት መቀንጨር ወደ 25 በመቶ ወርዷል፡፡ ይህ ትልቅ እመርታ ቢሆንም፣ አሁንም በኢትዮጵያ ከሚወለዱ 10 ህጻናት መካከል አራቱ የተመጣጠነ ምግብ ያለማግኘት ስጋት ውስጥ ናቸው ብሏል፡፡

በተመሳሳይ ወቅት ማለትም ከ1990 ዓ.ም. ጀምሮ ከ5ኛ ዓመት ልደታቸው በፊት የሚሞቱ ሕጻናት ቁጥር በሁለት ሶስተኛ እንዲሁም የእናቶች ደግሞ ከ100,000 እናቶች ወደ 191 አሽቆልቁሏል፡፡

በመግለጫቸው ወቅት ወ/ሮ ሜሌንዳ በቤተሰብ ምጣኔ፣ በጨቅላ ህጻናትና እናቶች ጤና አጠባበቅ ዙሪያ ድጋፋችን ይቀጥላል የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመቅረፍም አዳዲስ መንገዶችን ማበረታታችንንም አጠናክረን እንቀጥላለን፤ ምክንያቱም በጤና አጠባበቅ ዙሪያ የሚሞከሩ ማሻሻያዎች ዜጎችን ከድህነት ለማውጣት ቁልፍ መሳሪያ ናቸው ብለዋል፡፡

የሜሊንዳና ጌትስ ፋውንዴሽን ማንኛውም ሰው በጤናና በስኬት የመኖር መብት አለው በሚል መሰረታዊ መርህ ላይ የቆመ ፋውንዴሽን መሆኑን አሳውቋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com