ጥበብና ተፈጥሮ በወሎ! ወለዬዎች የተፈጥሮ ጠበቃዎች ናቸው?!

Views: 73

ዝግባ፣ ወይም በቅጽል ስሙ “አውሊያው” ጥብቅ ዛፍ፣ ወሎ በሚገኘው የአናቤ ጫቃ ውስጥ፣ ፎቶግራፉ ሲነሳ የተባበሩኝን አንድ የጀርመን ዜጋ እና ሌሎቹን ኢትዮጵያውያን፣ በጠቅላላ ስድስት ሰዎች፣አመሰግናለሁ።

ወሎ በብዙዎች አንደበት የውበት፣ የፍቅር ሃገር ተብሏል። ስለ ወሎ ሳስብ እኔን የሚያስገርመኝ እና የሚያስደምመኝ ደግሞ ተራራዎቹ፣ ኃይቁ፣ ከተማው፣ ምንጩ፣ ወንዙ፣ ወዘተ ሁሉ የተዘፈነለት መሆኑ ነው።

ለመሆኑ ወለዬዎች በአካባቢ ጥበቃ ምን ያህል ልምድ አዳብረዋል? በኢትዮጵያ የሚገኝ በስፋቱ ትልቅ ዛፍ ያየሁት ወሎ አናቤ ጫካ ውስጥ ነው፡፡ እንዲሁም ትላልቆቹን የጫት ዛፎች ያየሁት እዚሁ ጫካ ውስጥ መሆኑን አስታውሳለሁ። ወለዬዎች የተፈጥሮ ጠበቃዎች ናቸው?! ብዬ እገምታለሁ።

የጦሳን አቀበት ዝንጀሮ አትወጣውም፣

ሰው ከተፋቀረ እንከን አያጣውም፤

እባብ ዘለግላጋ እግር የለው እጅ፣

ጊዜ የጣለው ሰው የለውም ወዳጅ፡፡

አለ ተወዳጁ ዓለማየሁ እሸቴ በአምባሰል ሙዚቃው።

የጦሳን ተራራ ያየሁት በ፲፱፻፹ (1980) ዓ.ም ነበር። ቀጥ ያለ ግርግዳ፤ እውነትም ዝንጀሮ የማትወጣው። እንዲህ ነው እንጂ ሙዚቃ፡፡

እኛም አለን ሙዚቃ

ስሜት የሚያነቃ!!!

አሉ የቀድሞው የኦርኬስትራ ኢትዮጵያ ሙዚቀኞች።

በ፲፱፻፹ (1980) ዓ.ም በደቡብ ወሎ አናቤ የሚባል ጫካ ውስጥ በእንክብካቤ ተይዞ ያገኘሁትን የዝግባ ዛፍ ምስል ከዚህ ጽሑፍ ጋር አያይዧለሁ። በፎቶግራፉ የሚታየው የግንዱ ታችኛው ክፍል ነው። በጊዜው ለመለኪያ የሚሆን ማስመሪያ ወይም ሜትር (meter tape) ስላልነበረኝ አብረውኝ በመስክ ጥናት ላይ የነበሩትን ስድስት ሰዎች እጅ ለእጅ ተያይዘው እንዲቆሙ በማድረግ ነበር ወርዱን ለመለካት እና ለመገመት የቻልነው፣ በግምትም ፲፪ ሜትር ተኩል ይሆናል አልን።

ይህም እኔና ጓደኞቼ የኢትዮጵያን እጸዋት ስናጠና፣ ከዚህ ቀደም ያላጋጠመን የዛፍ ወርድ (ስፋት) ነበር። ከዚያ ጊዜ በኋላ፣ ዶክተር አሉላ ፓንክረስት ቦታው ድረስ ሄዶ ወርዱን ለክቶ የሚከተለውን ዘግቧል:

This tree was estimated by Prof. Mesfin to be about 12.5 meters in circumference and about 4 meters in diameter. True enough, when we measured the tree, we found it to be 12.7 meters in circumference. Is this then the largest tree in [the] Ethiopia? The tree is said to be 63 meters high. Is this figure correct? Has anyone seen a taller tree in this country? Forestry reports from the 1940s suggest a maximum height of 50 meters for Zegba trees, whereas reports in the 1990s suggest a maximum of 35 meters.

በኢትዮጵያ ትልቁ ዛፍ እንዲሁም ትልቅ ዕድሜ፣ በግምት ፰፻ (800) ዓመት፣ ያለው ይመስለኛል።

ታዲያ ቴዎድሮስ ካሣሁን ወለዬዎች ጠብቀው ያቆዩልንን ዛፍ “አንድ ፍቅር አጥተን ዝግባ የሚያሳክለን” ብሎ ሲያዜም፣ አንድነት- ፍቅር፣ አንድነት- ትልቅነት፣ አንድነት እንደ ትልቁ ዝግባ- መሆኑን ነው እያዝናና የሚያስተምረን፤ የሚያሳስበን።

ይህ ትልቅ ዛፍ ስለሚገኝበት ጫካ ሁኔታ በ፲፱፻፹ ዓ.ም በታተመ ጽሑፍ ውስጥ ይህንን ከአካባቢው ሰዎች ያገኘሁትን ስንኝ ጽፌነበር፡፡

አናቤ አረጀ አሉ ሽበት ደረደረ፣

አንድ ሰው ብቻውን ይሄደው ጀመረ።

በወቅቱ ጫካው እየሳሳ እና እየተመናመነ በመምጣቱ ምክንያት የአካባቢው ሰዎች የተሰማቸውን ስሜት የገለጹበት አድርጌ ቆጥሬው ነበር። ኋላ ላይ የዶክተር አሉላ ፓንክረስትን አንድ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፈን ጽሑፍ ስመለከት የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴን ጠቅሶ ለየት ያለ አመለካከት እንዳለ ተረዳሁ። ይህንን ነበር የጻፈው፡-

In An Illustrated Guide to the Trees and Shrubs in the Red Cross Project Areas in Wello (1989), Prof. Mesfin Tadesse mentions an Amharic saying about the forest, which Prof. Bahru translates in his article as: “Anabe is said to be growing old and greying, a solitary individual could now cross it without fear.” This may suggest, as Prof. Bahru notes that the forest has become denuded, although it may also refer to claims that shifta, outlaws, lived there in the past.”

ይህ ከላይ የተገለጸው ስንኝ በአጭሩ ሲታይ ቀደም ባለ ጊዜ አናቤ የሽፍታ ወይም የሽፍቶች መደበቂያ/መኖርያ እንደነበር በቅኔአዊ አነጋገር መገለጹ ነበር፡፡አሁን እንደሚታየው ለዚህ ተግባር ሊውል እንደማይችል-ም ነው የሚገልጸው።

የዶክተር አሉላን ጽሑፍ በሚከተለው ርዕስ እና አድራሻ ያገኙታል።

  1. Awliyaw: Medicinal Podocarpus Tree Largest and Oldest in Ethiopia?http://www.herbs.com/newdisplay.cgi?page=./HL/20000222-1.html February 22, 2000.

By Dr. Alula Pankhurst

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com