የህወሓት ከፍተኛ አመራር ከወደ አዴፓ ሰፈር ጋብቻ ሊመሠርቱ ነው

Views: 413

(በጥብቅ ሚስጥር የተያዘ)

 

  • ፖለቲከኛው የታዋቂ ድምፃዊት እህትን ነው የሚያገቡት፤
  • ጋብቻው እንዳይጸና ህወሓት ሳንካ ይፈጥራል ተብሎ ስለተሰጋ በጥብቅ ሚስጥር ተይዟል፤
  • የጋብቻው ሥነ-ስርዓት በአዲስ አበባና በባህር-ዳር ከተሞች ይፈጸማል፤
  • ጠ/ሚሩ በሠርግ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል!
  • ተጋባዦች ከካናዳ፣ አውሮፓ እና አሜሪካ ሀገር ውስጥ ገብተዋል!
  • “የራያ ሕዝብ ዕጣ ፋንታው ከአማራ ጋር ነው ብዬ አምናለሁ።አቶ ዛዲግ አብርሃ

 

የህወሓት ከፍተኛ አመራርና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት የራያው ወጣቱ ፖለቲከኛ አቶ ዛዲግ አብርሃ፣ ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ካሳወቁ በኋላ፣ በስደት (ለትምህርት) እንግሊዝ አገር አቅንተው እንደነበር እና በለውጡም ከጠ/ሚ ዐቢይ (ቲም-ለማ/ገዱ) ጋር ተደምረው ወደ መንግሥታዊ ሥራ (ሹመት) ተመልሰዋል፤ መንግሥታዊ የኮሙኒኬሽን (ፕሮፓጋንዳ) ሥራዎችን እያሳለጡ ነው፡፡

 

በዚህ ከህወሓት ወደ አዴፓ/ብልጽግና ፓርቲ ባደረጉት የፖለቲካ አሰላለፍ ዝውውር ሳቢያ፣ ከህወሓት ጋር ዓይንና- ናጫ ሆነው በ‹‹ሊገደሉ ይችላሉ›› ሥጋት በከፍተኛ ጥበቃ-ሥር ሆነው እንደሚንቀሳቀሱ ይታወቃል፡፡

 

እንዲያም ሆኖ፣ ቅዳሜ የካቲት 7 ቀን 2012 ዓ.ም በከፍተኛ ጥብቅ ሚስጥር የጋብቻ ሥነ-ስርዓታቸውን በአዲስ አበባ እና በባህር ዳር ከተሞች እንደሚፈጽሙ የኢትዮ-ኦንላይን የዜና ምንጮች የገለጹ ሲሆን፣ ህወሓት ጋብቻውን ያጨናግፋል ተብሎ ስለተሰጋ ፍጽጽሙ በቅርብ ቤተሰቦች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ጥቂት ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በሚስጥር (የሚዲያ ሽፋን ሳያገኝ) በከፍተኛ ጥብቅ ሥፍራ እንደሚፈጸም ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

አቶ ዛዲግ አብርሃ፣ ከህወሓት የፖለቲካ መንደር እንድገፋ ያደረገኝ የራያ ተወላጅ መሆኔ፣ ከብአዴን ሰዎች ጋር ያለኝ ቅርርብ እና ወጣትነቴ ነው ሲሉ የገለጹ ሲሆን፣ በዚህ ማንነታቸው በግል ህይወታቸውም የህወሓት አንጋፋ አመራር አባላት ጣልቃ ገብተው፣ በእጮኝነት ተቆራኝተዋት ከነበረው ሰማህል መለስ ዜናዊ ጋር እንዳነጣጠሏቸው የቅርብ ሰዎቻቸው ይገልፃሉ፡፡

 

(በወቅቱ የመለስ ዜናዊን ራዕይ አስፈጽማለሁ በሚለው የህወሓት/ኢሕአዴግ ቡድን እና ህወሓትን ከ‹‹ሴት ቀሚስ ተጽዕኖ›› እናላቅቃለን ብለው በተፃራሪነት ሲታገሉ የነበሩት ከጀርባ በአቦይ ስብሃት ነጋ እና በስውሩ የደህንነት ሰው አቶ ጌታቸው አሰፋ ይመራ በነበረው ቡድን) የቡድን መተጋገል የአቶ ዛዲግ እና የወ/ሪት ሰማህል መለስ ዜናዊ ግንኙነት (ፍቅር) መክሰሙን ምንጮች አስረድተዋል፡፡

 

አቶ ዛዲግ አብርሃ፣ ቅዳሜ የካቲት 7 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባና በባህር ዳር ከተሞች የጋብቻ ሥርዓታቸውን የሚፈጽሙት ከድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባሁ (ጂጂ) ታናሽ እህት ጋር ሲሆን (የዘማሪት ሶፊያ ሽባባው ታንሽ እህት)፣ ተጋባዥ እንግዶች ከካናዳ፣ ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን የኢትዮ-ኦንላይን ዘጋቢ አረጋግጧል፡፡

ይህ የጋብቻ ቁርኝት የተፈጠረው አቶ ዛዲግ አብርሃ ቀደም ሲል ጀምሮ ከም/ል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ከብአዴን/አዴፓ የአመራር አባላት እና ከጠ/ሚ አቢይ ጋር ባላቸው የሥራ ቅርርብ ሲሆን፣ በዚህ ሂደት መጀመሪያ የእጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)ን ታላቅ እህት ወ/ሮ ፍሬዓለም ሽባባውን ተዋውቀው፣ በእርሳቸው አማካኝነት ደግሞ ታናሽ እህታቸውን እንዳገኙና በፍቅር እንደወደቁ የኢትዮ-ኦንላይን የዜና ምንጮች ገልጸዋል፡፡

 

ቀደም ሲል ከህወሓት ጋር ተፈጥሮ የነበረው የመደብ-ጋብቻ ሂደት (ከሰማህል መለስ ዜናዊ) ጋር የነበረው የፍቅር ግንኙነት በተለያዩ የመደብና የርዕዮተ-ዓለም አሰላለፍ ከስሞ፣ በምትኩ ከወደ አዴፓ ሠፈር የታዋቂውን ነጋዴና ባለሃብት አቶ ሽባባው የመጨረሻ ሴት ልጅ ጋር ጋብቻቸው ሊፈጸም ቀናት ቀርተዋል፡፡

 

ለዚህ ጋብቻ መስመር በርከት ያሉ የአማራ ክልል ባለሃብቶችና ፖለቲከኞች በሽምግልናው ሂደት ላይ መሳተፋቸውን ዘጋቢያችን አረጋግጧል፡፡ ጋብቻው የራያ ህዝብን የማንነት፣ የባሕል፣ የሥነ-ልቦና ጥያቄዎችን ያማከለ ማኅበራዊ ፖለቲካ ነው ሲሉ ምንጫችን ለዘጋቢያችን አስረድተው እግዚአብሔር ከህወሓት ዓይንና ሤራ ይሰውርልን ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com