ከአቶ ታዬ ደንደአ መኪና ሁለት ሚሊዮን ብር የዘረፈው ተጠርጣሪ ተይዟል

Views: 211
  • ገንዘቡ በሥልጠና ላይ ላሉ አባላት ለአበል የተያዘ ነው
  • ማኅበራዊ ድረ-ገጽ ተጠርጣሪው እንዲያዝ ረድቷል ተብሏል!

 

ራሔል አናጋው

 

የብልጽግና ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ ታዬ ደንደአ በደብረዘይት/ቢሸፍቱ ከተማ ለአበል የያዙትን 2 ሚሊዮን ብርና የተለያዩ ንብረቶችን ዘርፎ ለመሰወር የሞከረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ዝርፊያው ከተፈጸመ በኋላ ተጠርጣሪው ግለሰብ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ‹‹ከተሰረቁት ንብረቶች የተወሰኑት በእጄ ላይ ደርሰዋል›› በማለት በራሱ ጊዜ በማሳወቁ ሊያዝ እንደቻለ አቶ ታዬ ደንደአ በተለይ ለኢትዮ ኦንላይን አስረድተዋል፡፡

ፖሊስም ይህን ግለሰብ ተከታትሎ ይዞ ምርመራ ጀምሮበታል ያሉት አቶ ታዬ ደንደአ ተጠርጣሪው ግብረአበሮች ሊኖሩት ስለሚችሉ ፖሊስ ክትትል እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ወንጀሉ የተፈጸመው ደብረዘይት ከተማ ላይ ሥልጠና ለሚወስዱ 400 ሰዎች የሚሆን የአበል ገንዘብ ከባንክ አውጥተን እየሄድን ነበር የሚሉት አቶ ታዬ፣ ‹‹ገንዘቡ እኔ ጋር የሆነበት ምክንያት የጥበቃ ሰዎች ስላሉኝ እና ፋይናንስ ሰዎች ጥበቃ ስሌላቸው በሚል ስጋት የመኪናው ኪስ ውስጥ ገንዘቡን አስገቡት፡፡››

ምሳ ልንበላ ‹‹ቢን ኢንተርናሽናል›› ሆቴል በወረድንበት ወቅት ነው የሆቴሉ ጥበቃዎች እንኳን እንዳይጠረጥሩ ሹፌር መስለው በተመሳሳይ ቁልፍ በመክፈት ንብረቱን የዘረፉት ሲሉ አቶ ታዬ ደንደአ ገልጸዋል፡፡

ጉዳዩን ፖሊስ ይዞታል፤ ከምርመራው በኋላ ሌሎች የሚመጡ ነገሮች ይኖራሉ ያሉት አቶ ታዬ፣ ጉዳዩ ስሮቆት ብቻ ላይሆን ይችላል፤ ፖሊስ በሂደት የሚያጣራው ይሆናል ሲሉ ለኢትዮ-ኦንላይን ገልጸዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com