ዘጠኝ ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

Views: 250

አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ መስፈረትን ያላሟሉ ምርቶችን ሲያመርቱ የተገኙ ዘጠኝ ፋብሪካዎቸ ላይ እርምጃ መውሰዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

 

እርምጃ ከተወሰደባቸው ፋብሪካዎች ውስጥ የሳሙና፣ የሲሚንቶ፣ የውኃ እና የወይን ፋብሪካዎች እንደሚገኙበት እና የ14 ፋብሪካዎች ናሙና የላብራቶሪ ውጤት እስከሚደርስ እየተጠበቀ መሆኑም ተገልጿል፡፡

 

ሚኒስቴሩ እንዳለው ቁጥጥር ከተደረገባቸው 185 ፋብሪካዎች ውስጥ ከ47 ፋብሪካዎች ላይ ወካይ ናሙናዎችን በመውሰድ የፊዚካል እና የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎባቸዋል፡፡

 

በላብራቶሪ ምርመራ ውጤቱ መሰረት የዘጠኝ ፋብሪካዎች ምርት ከደረጃ በታች በመሆናቸው ከማስጠንቀቂያ እስከ እሸጋ የሚደርስ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡

 

ሚኒስቴር መ/ቤቱ ባለፉት 6 ወራት 210 ፋብሪካዎች ላይ ቁጥጥር ለማድረግ አቅዶ በ185 ድርጅቶች ላይ ቁጥጥርና ክትትል አድርጌአለሁ ብሏል፡፡

 

ቁጥጥር ከተደረገባቸው 185 ፋብሪካዎች ውስጥ 162ቱ የኢትዮጵያን የጥራት ደረጃ መስፈርት ያሟሉ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com