ዜና

በአዲስ አበባ በወንበር ልክ ብቻ የሚጭኑ ፈጣን አውቶቡሶች ሥራ ጀመሩ

Views: 261

አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በተወሰኑ ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር ባለባቸው መሥመሮች ላይ በወንበር ልክ ብቻ የሚጭኑ ፈጣን 20 አውቶቡሶች ሥራ ማስጀመሩን አስታወቀ።

 

የድርጅቱ የኦፕሬሽን፣ ፋይናንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍሬው ሰማ እንደገለፁት፤ ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ አገልግሎት ላይ ያሉት እነዚህ አውቶቡሶች መነሻ ማዕከላቸው ከፒያሳ ሆኖ በአምስት መሥመሮች ይንቀሳቀሳሉ፡፡

 

መሥመሮቹ ከፒያሳ በሜክሲኮ ቄራ፣ ከፒያሳ በጦር ኃይሎች ዓለም ባንክ፣ ከፒያሳ በአምባሳደር ቦሌ፣ ከፒያሳ አዲሱ ገበያ ድል በር፣ ከፒያሳ ሽሮ ሜዳ መሆናቸውንም አቶ ፍሬው ገልፀዋል፡፡

 

አውቶቡሶቹን ልዩ የሚያደርጋቸው በወንበር ልክ ብቻ መጫናቸው፣ በእያንዳንዱ ፌርማታ የማይቆሙ እና ወጥ የሆነ የትራንስፖርት ታሪፍ የሚያስከፍሉ መሆናቸው እንደሆነ ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ሲል የዘገበው ድሬ ትዩብ ነው።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com