አዲስ አበባ ከተማ የግዢ አቅም ባለመፍጠሯ በጀቷን በአግባቡ መጠቀም ተሳናት

Views: 208

አዲስ አበባ ከተማ ባለፈው ዓመት ከምግብ ዋስትና ፕሮግራም ካፒታል በጀት ከተመደበላት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር፣ የግዥ አቅም ባለመፍጠሯ የተጠቀመችው 60 ሚሊዮን ብር ያልበለጠ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የከተማዋ አስተዳደር የልማታዊ ሴፍትኔት ኤጀንሲ ባወጣው መግለጫ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፈው ዓመት ከምግብ ዋስትና ፕሮግራም ካፒታል በጀት ከተመደበላቸው 1 ነይብ 3 ቢሊዮን ብር ውስጥ፣ የግዠ አቅም ባለመፍጠሯ 1 ነጥብ 24 ቢሊዮን ብር መጠቀም እንዳልቻለች ተመላክቷል፡፡

የከተሞች  ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና አስተባባሪ አቶ ደበበ ባሩድ እንደገለፁት በርካታ የማህበራዊ ልማት ችግሮች ያሉባት በመሆንዋ ምክንያት ከምግብ ዋስትና ከተመደበላት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የግዥህ አቅም ባለመፍጠሯ የተጠቀመቸችው 60 ሚሊዮን ብር ያልበለጠ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ባለፈው ዓመት የአዲስ አበባ ከተማ ከ 1 ቢሊዮን ብር በላይ የካፒታል በጀት ቢመድብለትም የተጠቀመው 6 በመቶ ብቻ መሆኑን ከዚህም የካፒታል በጀቱን ለትህምርት ቤት እድሳት፤ ለአቅመ ደካሞች ቤቶች ጥገና፤ ለህዝብ መፀዳጃና መታጠቢያ ቤቶች ጥገና ለውስጥ መንገዶች ግንባታ የሚውል ቢሆንም፣ የአለም ባንክ ክፍለ ከተሞች ለግንባታ የሚሆኑ ግብይቶችን አቅም የላቸውም በማለቱ 1 ነጥብ 24 ቢሊዮን ብር መጠቀም ሳይችል መቅረቱን አቶ ደበበ አብራርተዋል፡፡

የፌደራል መንግስት ደካማ በመሆኑ ምክንያትና በተደጋጋሚ በአፈፃፀም ችግር መተቸት የለብንም በሚል ኤጀንሲው በአሁን ሰዓት ኃላፊነቱን ወስዶ እየሰራ በመሆኑ፣ በአሁኑ ጊዜ 576 ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚያስችል ግብዓቶችን ለመፈጸም ጨረታ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com