በኢትዮጵያ 25 ሚሊዮን ህዝብ የንፁህ ውኃ አቅርቦት የለውም

Views: 262

በኢትዮጵያ በየትኛውም አካባቢዎች የሚገኙ የማሕበረሰብ ክፍሎች ንጹህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት የላቸውም፤ መንግሥት ይህን ችግር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡፡

የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ‹‹በገጠር የሚኖረው ማሕበረሰብ በቀን 25 ሊትር ውኃ በነፍስ ወከፍ እንዲያገኝ በከተማ የሚኖረው ደግሞ ከ 40 እስከ 100 ሊትር ውኃ በቀን ማግኘት እንዲችል እየተሰራ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

በዚህ ስሌት መሰረት የከተማዋ ነዋሪ 68 በመቶ እና የገጠሩ ነዋሪ ደግሞ 78 በመቶ የንፁህ መጠጥ ውኃ ማድረስ መቻሉንም ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል ውኃ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ዳሬክተር የሆኑት አቶ አስራት ካሳዮ  እንደገለጹት፣ በአማራ ክልል በከተማ 75 በመቶ፣ በገጠር ደግሞ 88 በመቶ የንፁህ መጠጥ ውኃ ሽፋን ማድረስ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

ከዚህም በፊት በገጠር አካባቢዎች ይሰሩ የነበሩ አነስተኛ የውኃ ተቋም የእጅ ጉድጓድና ምንጭ ማጎልበት ሲሆን፣ አሁን ላይ ግን ባለመስመር የሆኑ እስከ 15 ቀበሌዎችን የሚያገናኙ ትላልቅና ብዙ ሰዎችን የሚይዙ በመሆናቸው በቀን 25 ሊትር በሰው በመሆኑ፤ ሽፋኑን ባልተለመደ ሁኔታ አሳድጎታል፡፡

ይህም በከተሞች በቀን 20 ሊትር በሰው የነበረውን ስሌት አሁን ላይ ዝቅተኛው 40፣ ከፍተኛው ደግሞ 80 ሊትር አድርጎታል ተብሏል፡፡

በክልሉ ውኃ ተደራሽ ያልሆነባቸው ወረዳዎችና ባይኖሩም፣ ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑት እንደ ምስራቅ በለሳ ያሉ ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ ውኃ አለማግኘታቸው ተገልጿል፡፡

በቀጣዮቹ አምስት አመታትም የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦቱን በከተማም ሆነ በገጠር ተደራሽ ለማድረግ በድርቅ ተጋላጭ በሆኑ ቆላማ አካባቢዎች ከማህበረሰቡ በባለፈ ለእንስሳትም ጭምር ይሟላል ተብሏል፡፡

ለዚህም ስራ መፈፀም የሳውዲ መንግስትን ጨምሮ ከሌሎች አገራትና  ድርጅቶች ከ 600 ሚሊዮን ዶላር በላይ መገኘቱን ዶክተር ኢንጅነር ሽለሺ በቀለ ተናግረዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com