‹‹ወንዞቻችንን በከፍተኛ ሁኔታ መጠቀም ጀምረናል››

Views: 375

አሁን ወንዞቻችንን በከፍተኛ ደረጃ መጠቀም የጀመርንበት ወቅት ስለሆነ፣ ወንዞቻችንን ወደ ሚሄዱበት አካባቢ ከድንበር ተሻጋሪ ንግድ እና ከሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር የሚነሱ ጠንካራ ክርክሮች እንደሚኖሩ ይታወቃል ሲሉ የውኃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለጹ፡፡

እንደ ሀገራችን ሁኔታ ጥቅማችንን ለማስከበር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ልክ ለግድቡ እንደሚያደርገው አስተዋጽዎ ሁሉ፣ በዚህም ጉዳይ መጠነኛ ግንዛቤውን ይዞ መደገፍ የሚገባውን ነገር የመደገፍ አስተዋጽዎ ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡

ዶ/ር ኢንጅር ሲለሺ እንደተናገሩት ‹‹የሀገራችን ሀብት መሬትና ውሀ ነው፤ ከሁለቱ የሚገኙ ጥቅሞችን መጠቀም ካልቻልን ሀገራችንን ወደፈለግነው ደረጃ ማሸጋገር አንችልም፤ ስለዚህ እንደነዚህ አይነት ሀብቶችን ወደ ጥቅም ካላዋልን ሀገራችንን ከድህነት እናወጣለን የምንለው ነገር ከንግግር ያለፈ አይሆንም›› ብለዋል፡፡

ዓባይን የሚያክል ወንዝ ይዘን በቂ መሰረተ-ልማት ባለማልማታችን በወንዙ የሚገኘውን የኢኮኖሚ አቅም አጥተን ቆይተናል ያሉት ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ፣ አሁን ማድረግ ያለብን ትክክለኛ የሆነ ሁሉም የተፋሰስ ሀገሮች የውሃ አጠቃቀም ሕጎች በመጠቀም ማንም ሳይጎዳ ሁሉም ተጠቃሚ በሚሆንበት መንገድ ወስደን ውጤት ማምጣት ያስፈልገናል ሁሉም አሸናፊ በሚሆንበት መንገድ ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ ዘላቂ የሆነ የኤሌክትሪክና የውሃ አቅርቦት ለዜጎች ማቅረብ ይኖረብናል ይህ ሲሆን ነው ልማቱም ዘለቄታዊ የሚሆነው የዜጎች ማህበራዊ ህይወትም ከፍ የሚለው በማለት ‹‹ኢንስቲቲዩት ፎር ስትራቴጂክ አፌርስ›› የተባለ ተቋም በሀያት ሬጀንሲ ሆቴል ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ  አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ያላትን የውሃ ሀብት በአግባቡ አልተጠቀመችበትም፤ በርካታ ወንዞች በሀገራችን ቢኖሩም ለረጅም ዓመታት ለህዝቡ ተገቢውን ጥቅም ሳይሰጡ ሲፈሱ የኖሩ እና ለሀገራችን ሀብት ያልፈጠሩ መሆናቸው ግልጽ ነው ሲሉ የውኃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ መልክዓ ምድሯ ተራራማ ስለሆነ፣ የውሃ ማማ እንደሆነች ይታወቃል ያሉት ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ፤ ነገር ግን ያገኘችው ዝናብ በአጭር ጊዜ ውስጥ በወንዞቿ ተቀላቅሎ ጥቅም ሳይሰጣት ወደ ጎረቤት አገራት ይሄዳል ብለዋል፡፡

በአብዛኛው የአዋሽ ወንዝ፣ ተከዜ፣ ጥቁር አባይ፣ ገናሌ፣ ዳዋ፣ ዋቢሸበሌ እንዲሁም ከኦሞ ወንዝ በስተቀር ሁሉም በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ያሉ ወንዞች ድንበር አቋራጭ ናቸው ሲሉ ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ አስረድተዋል፡፡

‹‹በዓለም ላይ እንደነዚህ ዓይነት ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ያሏቸው አገራት ወንዞቹ ከሚሄዱባቸው አገሮች ጋር በመስማማት በጋራ መጠቀም ይኖርባቸዋል›› ብለዋል፡፡

በእኛ በኩል እንደ ሀገር ያሉንን ወንዞች ለማልማት ብዙ አልሄድንበትም፤ በሌላ በኩል በተለይም የዓባይ ወንዝ የሚደርስባቸው አገራት (ግብጽና ሱዳን) ውሃው በሙሉ የእኛ ነው ለሁለት እንክፈለውና እንካለፈል ብለው ለረጅም ጊዜ እንደራሳቸው መብት አድርገው ሲጠቀሙበት ነበር፤ በዚህ የተነሳ እንደ ወዳጅ ሳይሆን ጥሩ በማይባል መልኩ ብዙ ስንጨቃጨቅ ነው የኖርነው ሲሉ ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ ተናግረዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com