ወጣቶች 5 ሺ ሄክታር በመስኖ እንዲያለሙ ድርድር እየተካሄደ ነው

Views: 199

በጋንቤላ ክልል በሚገኘው የኦልዌሮ ግድብ ወጣቶች 5 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የመስኖ ልማት እንዲያካሂዱ የሚያስችል ድርድር እየተካሄደ ነው፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር ሚካኤል መሀሪ እንደገለፁት ኮሚሽኑ ወደ ልማት ባልገቡ እንዲሁም በከፊል ወደ ልማት በገቡ የመስኖ ፕሮጀክቶች ወጣቶችን በማሰማራት ዘመናዊን መስኖን በማራመድ  ምርታማነትን መጨመር በሚል አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በጋንቤላ ክልል በሚገኘው የኦልዌሮ ግድብ ወደ 10 ሺ ሄክታር መሬት ያለማል ተብሎ መገንባቱና ለ ወጣቶች 5 ሺ ሄክታር ተለይቶ እንደነበርም አስታውቀዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ ለሳውዲ ስታር የተሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፣ ተጨማሪ ድርድር የሚፈልግ ሆኖ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

ሳውዲ ስታር የራሱ ክፍተቶች ቢኖሩበትም፣ ባለፉት ዓመታት ያለማው ከ 800 ሄክታር አይበልጥም ያሉት ዶክተር ሚካኤል፣ መሬት የመንግስትና የህዝብ ሀብት ነው ሲሉም አስገንዝበው፣ ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com