በዐርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የጎርፍ አደጋ አደረሰ

Views: 56

በጋሞ ዞን በዐርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሰጎ እና የሲሌ ወንዝ በመሙላቱ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቆላ ሸሌ፣ ሸሌ ሜላ እና ኤልጎ ቀበሌዎች ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

ትላንት ጥር 25 ቀን 2012 ዓ.ም ሌሊት 11፡00 ሰዓት አካባቢ በተፈጠረው የጎርፍ አደጋ የመኖሪያ ቤቶች፣ የቤት ንብረት እንዲሁም ሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

ከዚህም ጋር በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ እየጣለ ባለው ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ በተከሰተ የመሬት ናዳ ምክንያት የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የዞኑ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ጽሕፈት ቤት ገልጿል ሲል የዘገበው አሐዱ ራዲዮ ነው።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com