በኢትዮጵያ አራት አዲስ ሰዎች በኖቭል ኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው እንደተገኙ ተገለጸ

Views: 399

በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ የ‹‹ኖቭል ኮሮና›› ቫይረስ አለባቸው ተብለው የተጠረጠሩ አራት ሰዎች እንደተገኙ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአሁኑ ወቅት አራት ሰዎች ማለትም አንድ ቻይናዊ እንዲሁም ሦስት ኢትዮጵያውያን የ‹‹ኖቭል ኮሮና›› ቫይረስ ተጠቅተዋል በሚል ምልከታ በክትትል ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የቫይረሱ ምልክት እንደታየባቸው የተገለጹት ሰዎች አንደኛው በአክሱም/ትግራይ እና ሦስቱ በቦሌ ጨፌ በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን፣ ናሙናቸው ተወስዶ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለበለጠ ምርመራ ለመላክ ዝግጅት መጠናቀቁንም የጤና ሚንስቴር አስታውቋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com