የልብ ሕሙማን ሕፃናት ቁጥር ከ 7 ሺህ በላይ ነው

Views: 194

ከማዕከሉ አመሰራረት በፊት ስለ የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማኀበር እንቅስቃሴ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ማኀበሩ ከተመሰረተ 30 ዓመት ሆኖታል፡፡ ከዚህም ውስጥ ለ20 ዓመት ያህል የሰራው ዘውዲቱ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ በሚገኘው ኮንቴይነር ውስጥ ነው፡፡ ከዛሬ አስር  ዓመት በፊት ደግሞ ጥቁር አንበሳ ሪፈራል ሆስፒታል ቅጥር ግቢ የሚገኘውን የልብ ሕሙማን ሕፃናት ሕክምና ማዕከልን ለማቋቋም በቅቷል፡፡

እያንዳንዱ የመኝታ ክፍል ደረጃውን የጠበቀ ነው፡፡ ማዕከሉ በዓመት ለ1,066 የልብ ሕሙማን ሕፃናት የቀዶ ሕክምና አገልግሎት የመስጠት አቅም አለው፡፡ አሁን ግን እየሰራ ያለው ከአቅሙ በታች በዓመት ለ450 ሕፃናት የተጠቀሰውን ሕክምና በመስጠት ነው፡፡

እስከ አሁን የእሥራኤል፣ የአሜሪካ፣ የእንግሊዝ፣ የህንድና የግብፅ ሕክምና ቡድኖች መጥተው ነፃ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በመስጠት ከርዳታቸውም በላይ የተረፋቸውን ግብዓቶች ማዕከሉ እንዲጠቀምበት ተባብረዋል፡፡ ወደፊት ደግሞ የደቡብ አፍሪካ በጎ ፈቃደኞች የሆኑ የሕክምና ቡድኖችን ለመጥራት ታስቧል፡፡

ማዕከሉ ለልብ ሕሙማን ሕፃናት የቀዶ ሕክምና አገልግሎት የሚሰጠው በነፃ ነው፡፡ ለቀዶ ሕክምና የሚውሉ ግብዓቶች ደግሞ በጣም ውድ ናቸው፡፡ ከዚህ አንፃር የማዕከሉ ቁልፍ ችግር የተጠቀሱት ግብዓቶችን ለማግኘት አለመቻሉ፡፡ ለመግዛት ቢያስብም ከአቅም በላይ መሆኑ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የልብ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት ለማግኘት ተመዝግበው ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ያሉት የልብ ሕሙማን ሕፃናት ቁጥር ከ7,000 በላይ ነው፡፡ የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች የሆኑ እነዚህ ሕፃናት ግብዓቶች ተገኝተውና ተራቸውም ደርሶ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት እስከሚያኙ ድረስ የሚሞቱም እንዳሉ መዘንጋት የለበትም፡፡ ይህ ዓይነቱም ሁንታ በእጅጉ ያማል፡፡

አቶ ሳላዲን ከሲሩ

የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን መርጃ ማኀበር ኘሬዚዳንት

ከሪፖርተር ጋዜጣ የተወሰደ

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com