ዜና

በሁለትና በሶስት ዓመት ውስጥ የተቆለለው ሕንፃ ተዘርፎ፣ ተሰርቆ፣ ኮንትሮባንድ ተነግዶ ነው

Views: 331

ኢህአዴግ በለያቸው ችግሮች በፀረ-ዴሞክራሲው ሕዝቡ ተሰቃይቷል ብለናል፡፡ ይህ የትግራይን ሕዝብ ይመለከታል፡፡ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ተፈፅመዋል ተብለናል፡፡ ይህ የትግራይን ሕዝብ ይመለከታል፡፡ ኢ-ፍትሃዊ የሆነ የሃብት ክፍፍል አለ ብለናል፡፡ግማሹ ፎቅ ሃያና ሰላሳ ሕንፃ ሲገነባ ጐዳና ተዳዳሪ ደግሞ አለ ብለናል፡፡ ይህ ደግሞ የተገነባው ላብ ጠብ ተደርጎ አይደለም፣ ተሰርቆ፣ ተዘርፎ ነው፡፡ በሁለትና በሶስት ዓመት ውስጥ የተቆለለው ሕንፃ ተዘርፎ፣ ተሰርቆ፣ ኮንትሮባንድ ተነግዶ ነው፡፡ የልማት ባንክ ገንዘብ ተወስዶ ነው፡፡ መሬት ተቀራምቶ ነው፡፡ ጨውና ፖታሽ ተቀራምቶ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ብዙ ነገር ተደርጎ ነው ብለናል፡፡

የብሄሮች ብሄረሰቦች ቋንቋቸው ተከብሮ፣ በቋንቋቸው እየተማሩና እየተዳኙ ባህላቸውንና ወጋቸውን እያሳደጉ ግን ደግሞ እነዚህ የተባበሩና ህብረት የሰሩ ማንነቶች አንድ የሚያደርጋቸው ቤት አለ፤ ይህም ኢትዮጵያነት ነው፡፡ ስለዚህ ህብረብሄራዊ አንድነቷ የጎላበት ኢትዮጵያን እንገነባለን እንላለን፡፡

ይህ ሲገነባ በመጀመሪያ የሚመጣው ጉዳይ የዜጎች ክብር ነው፤ ሁለተኛው ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያዊነታቸው በአገራቸው ከአገራቸውም ውጪ ሰው በመሆናቸው የግለሰብና የቡድን መብቶቻቸው የሚከበሩበት የዜጎች ክብር የሚጠበቅባት በሂደትም ግለሰባዊና ተቋማዊ ጭቆናዎች የሚወገዱበት እና ኢትዮጵያውያን በግለሰብ ደረጃ እንደ ግለሰብ በቡድን ደረጃ ደግሞ እንደ ቡድን የብሄር ቡድን፣ የኃይማኖት ቡድን፣ የፆታ ቡድን፣ የትምህርት ደረጃ ቡድን፣ ሌላ ማንነት በቡድን የሚገለፅባቸው የሚከበሩበት፣ የሚጎለብቱበት ነገር ግን የተናጠል የግለሰብ መብት ደግሞ የሚከበርበት ትሆናለች፡፡

 

አቶ ንጉሱ ጥላሁን

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኘሬስ ሴክራቴሪያት ኃላፊ

ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ የተወሰደ

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com