ባለወደቧ ትንሽዋ ጅቡቲ

Views: 305

ኢትዮጵያ ወደብ አልባ አገር በመሆኗ በተፈጠረው ሁኔታ በእጅጉ ተጠቃሚ የሆነችው ሀገር ጅቡቲ ስትሆን፣ ከቻይና ጋር በፈጠረችው ቅርርብና ትስስር ብዙ ርቀት ተጉዛለች፡፡ ሺንዋ የተባለው የቻይና የዜና አውታር ጥር 7 2012 ዓም በዘገበው መሰረት፣ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋንግ ይ፣ ከጅቡቲ ፕሬዚዳንት ከእስማኤል ኦማር ጉሌ ጋር ባደሩጉት ውይይት፣ በሁለቱ አገራት መሀል የተፈጠረው ግንኙነት ከፍተኛ ብልጽግና አንዳመጣ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም፣ አፍሪቃ ከሚገኙት ወደቦች መሀል አንዱ የሆነው የዶራሌ ወደብ፣ ነፃ ንግድ የመለዋወጫ ቀጠና (the Djibouti International Free Trade Zone (DIFTZ) የተባለውና፣ ከጅቡቲ አዲስ አበባ ድረስ የተዘረጋው የባቡር ሀዲድ ማስረጃዎች መሆናቸውን የዜና አውታሩ ጠቅሷል፡፡

ከሁሉም በላይ፣ ጅቡቲ ሰላም የሰፈነባት አገር ከመሆኗ ባሻገር፣ በጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ ምክንያት፣ ቻይና ለቀየሰችው የሀር ጎዳና (the silk – road) ተብሎ ሊሚታወቀው ከፍተኛ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፕሮጄክት አፍሪቃን በማገናኘት ሁነኛ ቦታ እንዳላት አውታሩ ዘግቧል፡፡ የሀር ጎዳና (the silk – road) በመባል የሚታወቀው፣ ከቻይና ተነስቶ በሩስያና አውሮፓ አቋርጦ አፍሪቃ ድረስ የሚዘረጋ የንግድ ቀጣና ሲሆን፣ ውጥኑን ከግብ ላማድረስ ስራው ተጀምሯል፡፡ ይህ ጎዳና የተዘረጋው በጥንት ዘመን ንግድ ይካሄድ የነበረበትን መስመር ተከትሎ ሲሆን፣ ለቻይናም ሆነ ጎዳናው ለሚያልፍባቸው አገሮችና ከተማዎች ጠቀሜታ ያመጣል ተብሎ ይገመታል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com