ዜና

አቶ ትዕግስቱ አወሉ ከፌዴራሊስት ኃይሎች ፎረም ምክትል ሊቀ መንበርነት እራሳቸውን አገለሉ

Views: 397

የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ሊቀ መንበር አቶ ትዕግስቱ አወሉ በህወሃት ጋባዥነት ትግራይ ክልል ሄደው የፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረም በመመስረት በምክትል ሊቀመንበርነት መመረጣቸውን የተናጉ ሲሆን፤ “ህወሃት እያካሄደ ባለው የሴራ ፖለቲካ ላለመሳተፍ ከፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረምና ምክትል ሊቀ መንበርነቴ እራሴን አግልያለሁ” ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

ዛሬ ከሃላፊነታቸውና ከፎረሙ ራሳቸውን ማግለላቸውን ያስታወቁት አቶ ትዕግስቱ፤ ግብዣው በተደረገበት ወቅትና ፎረሙ ሲመሰረት ዋና አላማ ያደረገው “ህገ መንግስቱ እየፈረሰ ስለሆነ እናድን፤ ፌደራሊዝም ስረዓቱም ወደ አሃዳዊነት እየተቀየረ ነው” በሚል መነሻ እንደነበረ አመልክተው፤ ይሁን እንጂ ፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረም ተብሎ እየተዋቀረ ያለው አደረጃጀት ፍፁም ዴሞክራሲያዊ ያልሆነና የቀድሞውን ያረጀ አስተሳሰብ ያነገበ መሆኑን በመረዳታቸው ከሃላፊነታቸውና ከፎረሙ መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።

“ይህ አካሄድ ቢመቻቸው እነርሱ የሚፈልጉት ብሄር ተኮር የሴራ ፌዴራሊዝም ካልተቻለ ደግሞ የመነጠል ፖለቲካ ይዘው መንቀሳቀስ ነው” ያሉት አቶ ትዕግስቱ፣ ህወሃት ያደራጀው የፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረም ገና ህጋዊ እውቅና እና ሰነድ ያላገኛ ከመሆኑም በላይ ትግሉን ለማካሄድ የሚፈልግበት መንገድ “የሃይል እርምጃን ጨምሮ ማንኛውንም አማራጭ እጠቀማለሁ የሚል ነው” ሲሉም ተናግረዋል።

በመሆኑም የአንድነት ፓርቲ አሁን እየተተገበረ ካለው ፖለቲካዊ ለውጥ ጎን “በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለአገርና ለህዝብ የሚጠቅም ፖለቲካ እሳተፋለሁ እንጂ ይህን የሴራ ፖለቲካ ልከተልም አልችልም” ሲሉ ለኢዜአ ተናግዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com