ዜና

የዓለም ዝንቅ ሕይወት

Views: 1937

ዝነኞች እና ቅንጡ የመኖሪያ ቤቶቻቸው

(ዓለምጸሐይ የኔዓለም  እና ፂዮን ናደው)

ዓለማችን በጉራማይሌ ሕይወት የተሞላች ናት፡፡ አንዱ እጅግ ተርፎት በምቾት ብዛት ተቀማጥሎ ሲታመም፣ ሌላኛው እጅግ ደህይቶ በማጣት ብዛት ታምሞ ይሞታል፡፡ ሁለቱ የማሕበረሰብ ክፍሎች ፍትሓዊ ትክክለኛነትን አስፍነው የዓለምን ሃብት ቢጋሩ፣ ሁለቱም የማኅበረሰብ ክፍሎች ከህመም ይድኑ ነበር የሚሉ የማህበራዊ ሳይንስ ልሂቃን አሉ፡፡

ይህን ኹነት በንጽጽር ትመለከቱ ዘንድ እውቅ የሆሊውድ ሰዎችን አኗኗርና ቅምጥል ቤቶቻቸውን እንቃኛለን፡፡

ለማነፃጸር ደግሞ ሌላ የአሜሪካን አገር ‹‹ጌቶ›› ሰፈር ወይም ወደ ህንድ ካልካታ ግዛት አናመራም፡፡ እዚሁ ያለንበት መንደራችን ውስጥ ያሉ ደሳሳ ጎጆዎችን ሕይወት መቃኘቱ ለንጽጽር በቂ ነው፡፡

እስቲቭ ሀርቬይ፡–

ዝነኛና የብዙ ተሰጥዖ ባለቤት የሆነው አሜሪካዊው እስቲቭ ሀርቬይ፣ በብዙዎች ዘንድ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞችን በመምራት ይታወቃል፡፡ እስቲቭ የአራት ልጆች አባትና የሦስት ልጆች የእንጀራ አባት ነው፡፡ ባለቤቱም ማሪ ጆሪ ትባላለች፡፡

 

የስቲቭ ሀርቬይ ቅንጡ የመኖሪያ ቤት 165 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል ተብሎ ይገመታል፡፡ ቤቱም አምስት ክፍሎችን፣ ቅንጡ የመዋኛ ገንዳ እና ቤተመጽሐፍትን ያካተተ ነው፡፡ ሥፍራውም ለእስቲቭና ለባለቤቱ ማሪ ጆሪ ለመኖር አመቺ ነው ተብሏል፡፡

እስቲቭ፣ የቴሌቭዥን ፕሮግራም አስተዋዋቂና ኮሚዲያን ከመሆኑም ባሻገር፣ የብዙ መጽሐፍት ደራሲም ጭምር ነው፡፡

ማት ለ ብላንክ፡-

ማት ለ ብላንክ፣ አሜሪካዊ ኮሚዲያንና የትወና ባለሙያ ሲሆን፣ በተለይም በቀድሞ friend’s ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ላይ እውቅናን አግኝቷል፡፡

በ2012 ፓስፊክ ፓራዳይዝ ከዘረዘራቸው ምርጥ ቅንጡ ቤቶች ውስጥ በዋነኝነት የእሱ ተጠቃሽ ነው፡፡ ቤቱም 4000 SQUARE FIT  የሚሸፍን ሲሆን፣ አራት የመኝታ ክፍሎችና ሦስት የመታጠቢያ ክፍሎችን ያካተተ ነው፡፡

ይህ ቅንጡ ቤት፣ የተወዳጅ የስፓኒሽ ቪላ አሰራር ዘዴ ያለው ሲሆን፣ መኖሪያ ቤቱንም ከሚስቱ ከተፋታ በኋላ በ 5.7 ሚሊዮን ዶላር  እንደገዛው ይነገራል፡፡ በአሁኑ የገበያ ተመን 8.75 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል ተብሎ ይገመታል፡፡ ብላንክ፣ በአሁኑ ጊዜ man with plan በሚል ተከታታይ ድራማ ላይ እየተወነ ይገኛል፡፡

ሳሙኤል ጃክሰን፡-

አሜሪካዊ ተዋናይ እና የፊልም አዘጋጅ የሆነው ሳሙኤል ጃከክሰን በ2018 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ታዋቂው Avengers ፊልም ላይ የትወና ብቃቱን አሳይቶል፡፡ የኒውዮርክ ኮንዶን ከዘረዘራቸው አሰወገራሚና ቅንጡ መኖሪያ ቤቶች መካከልም 13 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣው የሳሙኤል ቤት አንዱ ነው፡፡

 

 

ይህን ቅንጡ መኖሪያ ቤት 2005 ላይ 4.8 ሚሊዮን ዶላር የገዛ ሲሆን፣ ይህ ቤትም አራት የመኝታ ክፍሎችና ሦስት የመታጠቢያ ክፍሎች እንዲሁም የተገነባበት ወለል the LEONORI የሚባል አፓርትመንት ላይ አርፏል፡፡

ይህ ህንጻ፣ በ1900ዎች ውስጥ የተገነባ ቢሆንም፣ እስከ1980ዎቹ እምብዛም እውቅና ያገኘ አልነበረም፡፡ ነገር ግን፣ ከጊዜ በኋላ ወደ ቅንጡ መኖሪያ መንደርነት ተቀይሯል፡፡

ጃክሰን በአሁን ጊዜ በተለያዩ ፊለሞች ላይ ለመተወን እየተዘጋጀም ይገኛል፡፡ በተለይ ደግሞ THE BANKER ላይ በብቃት እየተወነ ይገኛል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com