በማእከላዊ ሶማሊያ የአዳዶ ከተማ ነዋሪዎች የአንበጣ ጣዕም ከዓሳ እንደሚበልጥ ገለጹ

Views: 386

በማእከላዊ ሶማሊያ የአዳዶ ከተማ ነዋሪዎች አንበጣን ከሩዝ እና ፓስታ ጋር በመቀላቀል እንደሚመገቡት የተናገሩ ሲሆን ጣዕሙም ከዓሳ እንደሚበልጥ ለኢትዮጵያ ዜና አገልሎት ድርጅት ገልጸዋል፡፡

በሶማሊያ በ 25 ዓመታት ታሪክ ውስጥ እጅግ የከፋ የአንበጣ መንጋ የተከሰተ ሲሆን አንዳንድ ሶማሊያውያን ይህ የበረሃ አንበጣ ጣፋጭ ምግብ እንደሆነላቸው ተናግዋል፡፡

ለሶማሊያ ቲቪ አስተያየቱን የሰጠው ሶማሊያዊ፣ አንበጣ የመድኃኒት ንጥረ ነገር አለው ብሎ እንሚያምን የገለጸ ሲሆን በዚህም የጀርባ ህመም እንዲሁም የደም ግፊቱን ለማስተካከል እንደሚመገበው ተናግሯል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ ድርጅት በበኩሉ በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች ላይ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በሰብሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን እና የቀጠናውን የምግብ ዋስትና አደጋ ላይ እንደሚጥል መጠቆሙን ቢቢሲን ዋቢ አድርጎ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com