ኢትዮ-ሳተላይት የታሰበላትን ምህዋር በመያዝ መረጃ መላክ ጀመረች

Views: 837

ETRSS-1 የተሰኘው የኢትዮጵያ የመረጃና ኮሙኒኬሽን ሳተላይት፣ በግማሽ ሰዓት ውስጥ ከመሬት 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ የሕዋ ምዋር ላይ ደርሶ ምድርን መቃኘት ጀምሯል፡፡

ዛሬ ታኅሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከማለዳው 12 ሰዓት ከ21 ደቂቃ በተሳካ ኹኔታ ወደ ሕዋ የመጠቀው የኢትዮጵያ ሳተላይት፣ ሥራ መጀመሩን የኢኖቬዥንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር አብስሯል፡፡

የሳተላይቱ የመረጃ መቀበያ ተቋም፣ እንጦጦ ላይ የተገነባ ሲሆን፣ ከማምጠቅ ሥራው ጀምሮ ቁጥጥሩ ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እየተከናወነ ይገኛል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com