ስለ ኢንዱስትሪ ፓርኩ የሀሰት ዘገባ ተሰርቷል ተባለ

Views: 315

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሠራተኞች የሚከፈለው ደሞዝ እና ጥቅማጥቅም በማነሱ ምክንያት ሊዘጋ ነው ተብሎ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተዘገበው ሀሰት እንደሆነ ተገለጸ፡፡

ዛሬ ታህሳስ 8 ቀን 2012 ዓ.ም በሀገሪቱ ባሉ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሠራተኞቹ የሚከፈለው ደሞዝ እና ጥቅማጥቅም በማነሱ ምክንያት ሥራ ወደ ማቆም ተቃርቧል ብሏል በሚል ተዘግቧል፡፡

ፓርኩ ሊዘጋ እንደንደሚችል የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ልማት ፓርክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሕመድ ሰዒድ መግለፃቸውንም ምክር ቤቱ እንደተጠቆመ ተደርጎ የተዘገበው ሀሰት እንደሆነ እና አቶ አህመድም እንደዚህ አይነት መረጃ እንዳልሰጡ ተጠቁሟል፡፡

‹‹የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሀገራችን አሉ ከሚባሉ ጠንካራ ፓርኮች መካከል አንዱ ነው፤ በፋይናንስ እጥረት ሊዘጋ ቀርቶ፣ እራሱን በማሳደግ ላይ ያለ ፓርክ ነው›› ሲሉ የኢትዮ ኦንላይን የመረጃ ምንጭ ተናግረዋል፡፡

ፓርኩ በአንድ ዓመት ከአራት ወራት ውስጥ ሰባት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመቱ ምርቶችን ለውጭ ገበያ አቅርቧል፡፡

አንድ ያለቀለት ሙሉ ሱፍ ልብስ ከኢንዱስትሪ ፓርኩ ሲወጣ፣ ከአምስት እስከ ስምንት የአሜሪካን ዶላር ዋጋ አለው፡፡ ይሄው ተመሳሳይ ምርት በዓለም ገበያ ግን ከሦስት መቶ እስከ አንድ ሺህ ሰባት መቶ የአሜሪካ ዶላር እንደሚሸጥ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com