ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ቴሌግራምን በስፋት ከሚጠቀሙ ሦስት አገራት ውስጥ አንዷ ነች

Views: 395
  • ‹‹ኋትስ አፕ›› (Whatsup) 1.6 ቢሊዮን
  • ፌስቡክ (Facebook) 1.3 ቢሊዮን ገደማ ተጠቃሚዎች አሏቸው!

በዓለም ላይ በስፋት ሰዎች ከሚጠቀሙበት የማኅበራዊ ሚዲያ ‹‹ፕላት ፎርም›› ውስጥ፣ አንዱ የሆነውን ቴሌግራም በከፍተኛ ደረጃ በመጠቀም ኢትዮጵያ አንዷ ነች ተባለ፡፡

ቴለግራምን በስፋት ከሚጠቀሙ የዓለም ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ፣ ኢራን እና ኡዝቤክስታን ብቻ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዓለም ላይ ሁለት መቶ ሚሊዮን ገደማ ተጠቃሚዎች ያሉት ቴሌግራም፤ በኢትዮጵያ ምን ያህል ተጠቃሚዎች እንዳሉት ግን የተባለ ነገር የለም፡፡

የማኅበራዊ ሚዲያ ‹‹ፕላትፎርም›› ከሆኑት ውስጥ በዓለማችን ብዙ ሰዎች የሚጠቀሙበት አንደኛው ‹‹ኋትስ አፕ›› ሲሆን፣ 1.6 ቢሊዮን ገደማ ሰዎች ይጠቀሙታል፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ፌስቡክ 1.3 ቢሊዮን ገደማ ተጠቃሚዎች እንዳሉት የዘገበው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com