ዜና

‹‹እንደትናትናው ሁሉ ዛሬም ሆነ ነገ አድነታችን ጸነቶ ያለና የሚኖር ነው›› – የቡራዩ ከተማ ነዋሪዎች

Views: 195

ከትናንት በስቲያ 14ተኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን አስመልክቶ የቡረዩ ከተማ ኗሪዎች ሕዝባዊ ውይይት አድርገዋል፡፡ በመድረኩ  ላይ ‹‹እንደትናትናው ሁሉ ዛሬም ሆነ ነገ አድነታችን ጸነቶ ያለና የሚኖር ነው›› ብለዋል ነዋሪዎቹ፡፡

በ2011 ዓ.ም. መጀመሪያ አካባቢ የተፈጠርው የዜጎች ከቀያቸው መፈናቀልና ግድያ ዳግም እንዳይከሰት የሁሉም ነዋሪዎች ፍላጎት መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ ከእውነት ይልቅ ስሜት ነግሶ ፤ከአንድነት ይልቅ ልዩነት ተሰብኮ ፤ማስተዋልን የጋረደ ብሎም የፖለቲካ ጥቅመኞች ትርክትና ተግባር የፈጠረው ክስተት ስለመሆኑም በቁጭት ተናግረዋል፡፡

ከተሳታፊዎች መካከል አቶ አህመድ ከድር የኢትዮጵያ ህዝብ ብዝሀነት ሳይወስነው  አብሮ የኖረ ይሁን እንጂ አንዳንድ ከማቀራረብ ይልቅ ማቃቃር ላይ የሚሰሩ መገነኛ ብዙሃን መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡ እነኝህ መገናኛ ብዙሃን ቁጥጥር ሊደረግባቸው እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡  አክለዉም፣ በአመራር እና በካቢኔዎች ላይ የሚታየዉ የአቋም መዋዠቅ ህዝብንም ሆነ ሀገርን የሚጎዳ ስለሆነ ሊታረም፣ሊጣራና፣በትክክለኛ የህዝብ አገልጋይነት አካሄድ ሊቃኝ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት አቶ ረታ ቶሎሳ በበኩላቸው ከግል ፍላጎት እና ስሜት ይልቅ አብሮነትን ብሎም እዉነትን እያስጨበጡ መጓዝ የግድ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የቡራዩ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ቃበቶ አልቤ በበኩላቸው እርሳቸውም የነዋሪወቹን ሀሳብ እንደሚጋሩት እና ከህዝብ የሚነሱትን ጥያቄዎች ለመመለስ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ ሃላፊው፣ የትኛዉም ብሄር፣ብሔረሰብና ሕዝብ ጥቅሙ ተከብሮ፤ በፍቅር፣በሰላም እና በአንድነት እንዲኖሩም አሳስብዋል፡፡

አሥራ አራተኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ዛሬ በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት በአዲስ አበባ ተከብሯል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com