ዜና

በአንገቷ ላይ ማተብ ያሰረች ህጻን ተወለደች

Views: 492

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዳንግላ ወረዳ በአባድራ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ውስጥ በአንገቷ ላይ ልዩ ምልክት (ማተብ) ያሰረች ህፃን መወለዷ ተገለጸ፡፡

የአባድራ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አዋላጅ ነርስ እውነቱ አብየ እንደገለፁት፣ ጥቅምት 27 ቀን 2ዐ12 ዓ.ም ከሌሊቱ 8፡ዐዐ አካባቢ በውፍታ ዳጢ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ጥሩወርቅ አብነት በአንገቷ ላይ የክርስትና እምነት ተከታዮች የሚያደርጉትን የማተብ ምልክት ያሰረች ህፃን መውለዳቸውን ተናግረዋል።

ህፃኗ ስትወለድ 3 ኪሎ ግራም የምትመዝን ሲሆን፣ አሁን ላይ ህፃኗም ሆነ እናቷ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

የህፃኗ እናት ወይዘሮ ጥሩወርቅ አብነት “ስትወለድ ክስተቱ አስደንግጦኝ ነበር፤ አሁን ግን ልዩ ማተብ አድርጋ የተወለደች ህፃን ልጅ እናት ስለሆንኩ ደስተኛ ነኝ” ብለዋል፡፡
(ዘገባው የአማራ ብዙሀን መገናኛ ነው)

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com