ዜና

ኢትዮጵያዊቷ ፍሬወይኒ መብራህቱ የሲኤንኤን የዓመቱ ጀግኒት ሽልማትን አሸነፈች

Views: 308

በትናንትናው ዕለት በኒውዮርክ ከተማ ይፋ በሆነው የሲ ኤን ኤን የአመቱ ጀግኒት (hero of the year) ሽልማት፤ ከአስር እጩዎች መካከል ፍረወይኒ መብራህቱ አሸንፋለች።

ተሸላሚዋ የወር አበባን ማዕከል በማድረግ በመቀሌ ከተማ ማርያም ሰባ የተሰኘ የሚታጠብ የሴቶች የንፅህና መጠበቂያን በማምረት ሥራ ላይ ተሰማርታ በማገልገል ላይ ትገኛለች።

በእለቱ ሽልማቷንም ከተቀበለች በኋላ ስሜት በተቀላቀለበት መንፈስ ሲኤኤንን አመስግናለች። “ይሄ ለኔ ብቻ ሳይሆን፤ ለሁሉም ሴቶች ነው። የወር አበባ ቃሉን ለመናገር እንኳን ስንሸማቀቅበት ኖረናል።

ሲኤንኤን ሥራዬን እውቅና በመስጠት በወር አበባ ላይ ውይይቶች እንዲኖሩ አስተዋፅኦውን አድርጓል” ብላለች።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com