ዜና

ግምታዊ ዋጋው ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ዋለ

Views: 209

የገቢዎች ሚንስተር ከ28 ሚሊዮን 386 ሺህ ብር በላይ የሚገመት አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡

አደንዛዥ እፁ፣ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በዓለማቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ዴስክ በትናንትናው እለት በጉምሩክ ኢንቴሌጀንስ ሰራተኞች እና በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኖምዛሞ ግላዲየስ ቦዛ የተባለች የደቡብ አፍሪካ ዜጋ መነሻዋን ከደቡብ አፍሪካ መዳረሻዋን ወደ ህንድ ደልሂ በማድረግ 7.4 ኪሎ ግራም ኮኬይን ስታዘዋውር በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡

በእለቱም ግምታዊ ዋጋው ከ28 ሚሊዮን 386 ሺህ ብር በላይ የሚሆን በድምሩ 11 ነጥብ 4 ግራም ኮኬይን በቁጥጥር ስር መዋሉን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com