ዜና

የህወሓትን ግብዣ ፓርቲዎች አልተቀበሉም

Views: 302

‹‹ፌዴራል ሥርዓቱንና ሕገ-መንግሥትን መጠበቅ›› በሚል መርህ በህወሓት አስተናባሪነት በመቀሌ ከተማ በተካሄደ ውይይት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ የተደረገላቸው ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ግብዣውን ውድቅ ማድረጋቸውን አሳወቁ፡፡

በመቀሌ ከተማ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተካሔደው የውይይት መድረክ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ከቀረበካቸው ተፎካካሪ ፓርቲዎች አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች ጥሪውን አለመቀበላቸውን አሃዱ ኤፍ ኤም ነው የዘገበው፡፡

ጥሪውን ውድቅ ካደረጉ ፓሪቲዎች መካከል አንዱ የአሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ነው፤ “ህውሐት ከዚህ በፊት የፌደራል ሥርዓቱን በሥርዓት ሲመራ ስላልነበር፣ ዛሬ የፌደራል ሥርዓቱ ተቆርቋሪ ነኝ ማለቱ የሚታመን አይደለም” ብለዋል የፓርቲው የወጣቶች ዘርፍ ተጠሪ አቶ አዲሱ ቡላላ፡፡

ሌላው ጥሪውን ውድቅ ያደረገው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ “ከዚህ በፊት እኛን ሲያሳድድ  ከነበረ ኃይል ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሊኖረን አይችልም” ብላው ከጥሪው ቀርተዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com