እነ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ የ214.4 ሚሊዮን ብር አዲስ ክስ ተመሰረተባቸው

Views: 50

የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኛውን ጨምሮ፣ በአራት ተጠርጣሪዎች ላይ የ214.4 ሚሊዮን ብር አዲስ ክስ ተመሠረተ፡፡

የመከላከያ ሚኒስቴርን መመርያ በመጣስ ግምቱ 241,443,021 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የጦር መሳሪያ ራዳር ግዥ በመፈፀም፣ በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል በማለት ነው ክሱ የቀረበው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ግዥውን የፈፀሙት ከቻይናው ኩባኒያ ጋር ያለ አግባብ ውል በማድረግ ብሎም ከቻይና ናሽናል ኤሌክትሮኒክስ አስመጪ እና ላኪ 8.6 ዶላር፣ ከኤሮስፔስ ሎንግ ማርች ኢንተርናሽናል ትሬዲ ኩባንያ ደግሞ 10.25 ሚሊየን ዶላር የራዳሮች ግዥ ማድረጋቸውን አቃቤ-ሕግ በክሱ አስረድቷል፡፡

የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32 (1ሀ) እንዲሁም 411 (1ሐ) እና (3) የተደነገገውን በመተላለፍ የኮርፕሬሽን የግዥ መመርያን ወደ ጎን በመተው ያለ ጨረታ ሚንስትር መስርያ ቤቱ ሁለት የቻያን ኩባንያዎች 111 ራዳርዎች ግዥ እንዲፈፀም አድርጎል ብሎ የፌደራል አቃቤ-ሕግ ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 18ኛ ወንጀል ችሎት ለኅዳር 30 ቀን 2012 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ክሱ የተመሰረተባቸው የቀድሞ የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ የሃይቴክ ኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጅ ሌተናል ኮሎኔል ፀጋዬ አንሙት፣ የቦርድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ  የሆኑት ኮሌኔል ሸጋው ሙሉጌታ እና የስነ-ምግባርና የሕግ ጉዳዮች ኃላፊ የነበሩት ኮሎኔል መሀመድ ኢብራሂም መሆናቸው ታውቋል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com