‹‹በአሀዳዊነት እና በአንድነት ዙሪያ ግራ መጋባት አለ››

Views: 54

‹‹በአሀዳዊነት እና በአንድነት ዙሪያ ግራ የመጋባት ነገር ያለ ይመስላል›› ሲሉ የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ተናገሩ፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራችን በዚህ ወቅት አንድነት ትፈልጋለቸች፤ ያለ አንድነት ይቺ ሀገር ወደ ፊት መሄድ አትችልም፡፡

በአንድነት ግን ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የራሳቸውን ህመም ብቻ ከመስማት፣ የሌሎችንም ችግር ሰምተው፤ የመፍትሄ ሀሳብ የማቅረብ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡

የሶማሌ ክልል አስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ለኢቲቪ እንደተናገሩት አሀዳዊነት ማለት የመንግሥትን የውሳኔ አሰጣጥ ወደ አንድ ቦታ ሲያመጣ ነው፡፡

በጣም በርካታ ባሕሎች፣ እምነቶች፣ ቋንቋዎች፣ የአኗኗር ዘይቤዎች እና ሥርዓቶች ባሉባት ሀገር፣ አሀዳዊነት ተመራጭ የአስተዳደር ስልት ሊሆን እንደማይችል አስታውቀዋል፡፡

‹‹በሶማሌ ክልል ባለፉት 27 ዓመታት ትክክለኛ ፌደራሊዝምም ሆነ ዴሞክራሲ አልነበረም፤ ብዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲፈጸሙ እንደነበር ግልፅ ነው›› ያሉት አቶ ሙስጠፌ፣ ‹‹ስለዚህ፣ እንዴት ያልነበረውን ፌዴራሊዝምና ዴሞክራሲ ውህዱ ፓርቲ አሀዳዊ ሆኖ ሊያመጣው ይችላል›› ሲሉ ጥያቄውን በጥያቄ መልሰዋል፡፡

አሀዳዊነት የሚባለው ለምሳሌ የሶማሌ ክልል የራሱን ክልል የማስተዳደር መብቱን ለሌሎች አሳልፎ ሲሰጥ እና ሶማሌ ያልሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎ የክልሉ ህዝብ በዚህ መልኩ መተዳደር አለበት የሚሉ ከሆነ ነው አሀዳዊነት የሚመጣው፡፡

አሁን ያየነው የውህደት ፕሮግራም ላይ ደግሞ ይሄን አላየንም፤ በአሀዳዊነት ላይም ብዙ ተወያይተናል ብለዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃም ይሁን በሶማሌ ህዝብ ላይ ውህደቱ አሀዳዊነትን በማምጣት የብሔር ብሔረሰቦችን መብት ያፍናል የሚል ውዥንብር ሲፈጠር ህዝባችን ጋር ሄደን ስለ ውህደቱ እንዴት እንደሆነ  አስረድተን ብንመጣ ይሻላል በማለት ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ የክልሉ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገናል፡፡

በውይይቱ እንዳወቅነው፣ ውህደቱ እስካሁን የሶማሌ ህዝብ አግኝቶት የማያውቅ በሀገሩ ላይ የመወሰን ነጻነት እንዲያገኝ ስላደረገው ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቷል ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com