በጤናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ አገልግሎት የሚሰጡ ኩባንያዎች ከ60 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ አገኙ

Views: 47

በጤናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ አገልግሎት የሚሰጡ ኩባንያዎች፣ ከ60 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ አገኙ፡፡

በኢትዮጵያ ለሚገኙ ለመንግሥት እና የግል ህክምና ማዕከላት እንዲሁም ለክሊኒኮች በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ግልጋሎት ለማቅረብ ለሚያስቸሉ አገልግት ሰጪ ኩባንያዎች የ63 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

በኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር እና በአሜሪካ መንግሥት ትብብር የተደረገው ይህ ስምምነት ጀማሪ ተቋማትን ለመደገፍ የሚያስችል የመነሻ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ በማስብ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ስምምነቱ የተካሄደው አርቢትሊ ኩባንያ እና አጋሩ ኢኤልዝ አይቲ ሰርቪስስ (ኦርቢት ሔልዝ) በተሰኘው ተቋም፣ እንዲሁም ከሳቫና ቬንቸር ካፒታሊስት ፈንድ ተጠቃሽ ከሆኑት መካከል ሳቫና ቬንቸር ፈንድና መቀመጫውን አሜሪካ በሆነው ‹‹በጣም ግሩፕ›› የተሰኛ በውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የተቋቋመ ኩባንያ መካከል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የበጣም ግሩፕ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፉዚዮን ቸርነት እንደገለፁት፣ በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ መሠረት ያለው የጤና ዘርፍ እንዲፈጠር ጀማሪዎች የተጠናከረ አቅም ላይ እንዲደርሱ የሚያስችል ድጋፍ እንደሚያሻቸው አብራርተዋል፡፡

የአሜሪካ መንግሥት የፈቀደው ድጋፍ አርቢትሊ ተቋም በጤናው መስክ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት በአገሪቱ የሚገኙ የጤና ተቋማት ቀልጣፋ አገልግሎቶች እንዲሰጡ ማስቻል መሆኑን የዘገበው ሪፖርተር ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com