መንግሥትን የ“ወርቃማ አክሲዮን” ባለቤት የሚያደርግ ረቂቅ ዓዋጅ ፀደቀ

Views: 53

 መንግሥት የ”ወርቃማ አክሲዮን” ባለቤት ሆኖ፣ የልማት ድርጅቶችን እዲሸጥ የሚፈቅድ ረቂቅ ዓዋጅ ጸደቀ፡፡ ዓዋጁ የፀደቀው የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ ኅዳር 20 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ነው፡፡

የዚህ ረቂቅ የሕግ ሠነድ ስያሜ “ረቂቅ የፕራይቬታይዝ ዓዋጅ” ሲሆን፣ ረቂቅ የሕግ ሠነዱንም ያዘጋጀው የገንዘብ ሚኒስትር ነው፡፡

“ወርቃማ ዓዋጅ” ማለት መንግሥት የልማት ድርጅቶችን በመለወጥ የካፒታሉ አካል የሆነና በማናቸውም የቦርድ ውሳኔ ላይ ድምፅ የመስጠትንና ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቶችን ለመንግሥት የሚያጎናፅፍ፣ በአክስዮን መመስረቻ ጽሑፍ የተደነገጉ ልዮ መብቶችን የያዘ አክሲዮን ነው ሲል አትቷል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት በበኩሉ ባወጣው መረጃ ምክር ቤቱም በቀረበለት ረቂቅ ዓዋጅ ላይ በመወያት አፅድቆ ሕግ ሆኖ እንዲወጣ ለህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት መላኩን ገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም መንግሥት በሙሉና በከፊል እንዲሸጡ ውሳኔ ካሳለፋበቸው የልማት ድርጅቶች መካከል ኢትዮ ቴሌኮም፣ የስኳር ፋብሪካዎች፣ የኃይል ማመንጫዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደሚገኙበት የዘገበው ሪፖርተር ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com