ኢሕአዴግ እንዲዋሃድ የሶማሌ ክልል አስተዳዳሪዎች ጠይቀዋል

Views: 38

ከዚህ በፊት የነበሩ ሁሉም የሶማሌ ክልል አስተዳዳሪዎች፣ ኢህአዴግ እንዲዋሀድ ጥያቄ ሲያቀርቡ እና ግፊት ሲያደርጉ ነበር የቆዩት ሲሉ የሶማሌ ክልል አስተዳደር ገለጸ፡፡

‹‹የሶማሌ ክልል ህዝብ የተገፋ ህዝብ ነው ብለን ስለምናምን እኛ ስንመጣም ከዛው ነው የቀጠልነው፤ ህዝቡ ኢትዮጵያዊነቱን የሚያረጋግጠው እራሱን በራሱ ማስተዳደር በመቻሉ ብቻ ሳይሆን፣ መሐል ሀገር መጥቶ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በሀገር ጉዳይ ላይ መወሰን ሲችል ነው የሚል እምነት አለን›› ሲሉ የክልሉ ም/ል ፕሬዝዳንት ተናግረዋል፡፡

ይህንን ሀሳብ በመያዝ ሀዋሳ ላይ በኢህአዲግ ጉባዔ ውህደቱ ጸድቆ ከተመለሱ በኋላ፣ በክልሉ ፓርቲ (ሶህዴፓ) አመራሮች ላይ ምንም ልዩነት ሳይኖር ውህደቱን በሙሉ ድምጽ ማጽደቃቸውን የተናገሩት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ናቸው፡፡

በሰዓቱ የውህዱ ፓርቲ ፕሮግራምና ሕገ ደንብ ገና ወጥቶ ስላለቀ ውህደቱ ምን አይነት ቅርጽ ሊይዝ እንደሚችል ስላልታወቀ እና ግልጽ ስላልነበር በመርህ ደረጃ ብቻ በመቀበል ወደ ፓርቲ ሙሉ ለሙሉ ለመግባት ፕሮግራሙንና ሕገ ድንቡን ስናይ ነው በማለት በማዕከላዊ ኮሚቴም በክልል ስራ አመራር ደረጃም መወሰናቸውን ገልጸዋል፡፡

ቀጥሎም በአዲስ አበባ በውህዱ ፓርቲ ፕሮግራምና ሕገ ደንብ ላይ ውይይት ሲደረግ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ያሉንን ጥያቄዎች በሙሉ አቅርበን ተቀባይነትም አግኝተናል ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com