‹‹የብልጽግና ፓርቲ አይጠቅምም ካሉ ለምን ጠቃሚ አማራጭ አያቀርቡም?!›› – የሶማሌ ክልል ም/ል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ

Views: 491

አዲሱ የብልጽግና ፓርቲን ሀሳብ መጥፎ እና የማይጠቅም ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች፣ አማራጭ የሆነ የፖለቲካ ሀሳብ (ፍልስፍና) ማምጣት አለባቸው ሲሉ የሶማሌ ክልል ም/ል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ተናገሩ፡፡

‹‹እንደ ፖለቲካ ተፎካካሪ የመዋሀድ ሀሰብ ለሀገራችን አይጠቅምም የሚል አካል ካለ፣ ከመከፋት ይልቅ ደስ ሊለው ይገባል፤ ምክንያቱም ተቀናቃኛቸው ጥሩ ሀሳብ ይዞ ካልመጣ የፖለቲካ መሰናክሎችን በመፍጠር ለመጣል ከመሞከር ይልቅ የተሻለ ሀሳብ በመያዝ ተደራጅቶ መፎካከር ይሻላል፤ መሰናክል በመፍጠር ሞቼ እገኛለሁ ማለት ሀሳቡን እንደፈሩት መናገር ማለት ነው ብዬ አስባለሁ›› ብለዋል፡፡

ከሶማሌ ክልል አንጻር፣ አሁን የተደረገው መዋሀድ ይጠቅመናል እንጂ አይጎዳንም፤ እኩልነት ያሰፍናል፣ ድምጻችን እንዲሰማ ያደርጋል፣ መሐል መጥተን ሀሳባችንን እንድናካፍል ስለሚረዳን ደስተኞች ነን ብለዋል፡፡

በሀገራችን ‹‹መደመር›› የሚል አዲስ የፖለቲካ ፍልስፍና ተፈጥሯል ‹‹ብልጽግና›› የሚል አዲስ የፖለቲካ መሳሪያ ደግሞ ተፈጥሯል፡፡

ይህ ሀሳብ በአንድ ወገን የቀረበ ነው፤ እኛ ሀገር ግን የሚታየው ነገር የአንዱን ሀሳብ በኃይል ለማስቆም በመበጣበጥ፣ የሀይማኖት ጦርነት በማስነሳት፣ የብሔር ግጭት በማስነሳት ነው የሚያምነው፡፡

የሀገራችን ፖለቲካ ያ ከሚሆን፣ መድረኩ ክፍት ስለሆነ፤ አሁን የተቀመጠው አቅጣጫ ትክክል ስላልሆነ የራሱን የፖለቲካ ፍልስፍና ሰርቶ እና የፖለቲካ አደረጃጀት አዘጋጅቶ ወደ ውድድርና ወደ ህዝብ መሄድ ነው፤ አሸናፊው ሀሳብ ይለያል እንጂ፣ ያንን ሀሳብ ለማስቆም ሀገር መበጥበጥ ጠቃሚ አይደለም ብለዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ በመደመር ፍልስፍ ላይም ብዙ ትችቶች ይቀርባሉ፤ ትችቶቹ ግን የፍልስፍናው ዋና ሀሳብ ላይ ሳይሆን፣ አብዛኛውን ግዜ ትችቱ ያለው ቃሉ ላይ፣ ወይ ጸሐፊው ላይ ነው ሲሉ አቶ ሙስጠፌ ተናግረዋል፡፡

‹‹ፍልስፍናው እንከን የለሽ ነው ማለት አይደለም፤ ነገር ግን፤ ከመጽሐፉ ላይ የሚተች ነገር ካለ፣ እሱን አውጥቶ ይሄ ይሄ ትክክል አይደለም ተብሎ ቢተች ደስ ይላል›› ብለዋል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com