ዜና

‹‹ውህዱ የብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልልን መብት የሚጋፋበት ነገር የለም›› – የሶማሌ ክልል አስተዳደር

Views: 277

የሶማሌ ክልል በውህዱ የብልጽግና ፓርቲ የሚኖረው አደረጃጀት፣ የፌዴራል መንግሥትን መዋቅር የተከተለ እንደሆነ፣ የሶማሌ ክልል አስተዳደር አስታወቀ፡፡ ፓርቲው በፌዴራል ደረጃ፣ በክልል ደረጃ እና በዞን ደረጃ ቢሮ ይኖረዋል ሲል የሶማሌ ክልል አስተዳደር አስታውቋል፡፡

ውህዱ ፓርቲ የክልሉን መብት የሚጋፋበት ምንም አይነት ነገር የለም፤ ከአሰራር ውጪ የሚመጡ የህዝቡን መብት የሚጋፉ ነገሮች ካሉ ደግሞ፣ የክልሉ አመራርና የፌዴራል አመራሮች ኃላፊነቱን ወስደው ተነጋግረው ያስቆሙታል ብለዋል፡፡

አብዛኛውን ጊዜ አላስፈላጊ ትኩረት በወረቀት ላይ ለሰፈረ ነገር ይደረጋል ያሉት የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ፣ በወረቀት ላይ ግልጽ የሆነን ነገር በፌዴራልም ሆነ በክልል ያለ አመራር በቁርጠኝነት በማስከበር ዋስትና ካልሰጠው ትርጉም እንደሌለው አቶ ሙስጠፌ ገልጸዋል፡፡

‹‹የፓርቲው ሕግና ደንብ በወረቀት ላይ ስለሰፈረ ብቻ ዋስትና ሊሆን አይችልም፤ ዋስትና ከወረቀት ብቻ የሚገኝ ቢሆን ኖሮ፣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ለሰላሳ ዓመታት የጻፋቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ፤ እነዛ ሁሉ በተከበሩ ነበር›› ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com