ዜና

የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ ያለስምምነት ተበተነ

Views: 213

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ዛሬ ኅዳር 19 ቀን 2012 ዓ.ም ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በፓርቲዎች የምዝገባና የስነ ምግባር ዓዋጅ  ማስፈፀሚያ ደንብ ዙሪያ እያካሄደው የነበረው ውይይት ባለመግባባት ተበትኗል።

ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጸደቀው ዓዋጅ ማስፈጸሚያ ደንብ ላይ ለመወያየት በምርጫ ቦርድ አማካኝነት ቢሰበሰቡም፣ ሳይስማሙ በመቅረታቸው ውይይቱ ሊቋረጥ ችሏል።

በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጸደቀው ዓዋጅ ብዙ ፓርቲዎች ያልተስማሙበት ሃሳቦች አሉበት በማለት ከፍተኛ ክርክር እንዳዳረጉም ለማወቅ ተችሏል።

ፓርቲዎቹ በሦስትና አራት ቀናት ውስጥ ያላቸውን ጥያቄ ለምርጫ ቦርድ እንዲያቀርቡም መጠየቃቸውን ለማወቅ ተችሏል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com