ዜና

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ለስድስት ግለሰቦች አዳዲስ ሹመቶችን ሰጠ

Views: 202

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት፣ ለስድስት የአመራር አባላቱ ሹመቶችን መስጠቱትን አስታወቀ፡፡

በዚህም መሠረት አቶ ፍቃዱ ተሰማ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፤ አቶ አዲሱ አረጋ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ፣ የማሕበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ፤ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ፣ የምጣኔ ኃብት ዘርፍ አስተባሪ፤ አቶ ካሳሁን ጎፌ የኦሮሚያ ገቢዎች ባለስልጣን ኃላፊ፤ አቶ ሳዳት ነሻ በኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የከተማ ፖለቲካ አደረጃጀት ኃላፊ፤ እንዲሁም አቶ አበራ ወርቁ በኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል፡፡

የኢሕአዴግን መክሰምና የብልፅግና ፓርቲ መመስረትን ተከትሎ፣ የኢሕአዴግ አጋርና ግንባር ድርጅቶች ራሳቸውን በማክሰም ላይ ናቸው፡፡

በመሆኑም፣ አዳዲስ አደረጃጀቶች እየተፈጠሩ ስለሆነ፣ በሁሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ማዕከሎች አዳዲስ ሹመቶች እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

ይሁን እንጂ፣ የክልል መንግሥታትም ሆኑ የፌዴራል መንግሥት የፓርቲ ኃላፊዎችን የመሾምም ሆነ የመሻር ሥልጣን የላቸውም፤ ኃላፊዎችን የመሾምም ሆነ የመሻር ሥልጣን የፓርቲው ሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ ነው ሲሉ አካሄዱ ላይ ሂስ የሚያቀርቡ አካላት አሉ፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com