ዜና

የአዲስ አበባ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ማካሄድ ጀመረ

Views: 198

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ምክር ቤት፣ ሰባተኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ማካሄድ ጀምረ፡፡

ጉባዔው በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን፣ ነገም ቀጥሎ የሚውል መሆኑ ታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀመን ይገመግማል ተብሏል፡፡

የትምህርት ቢሮ፣ የቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ፣ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃይል ልማት ቢሮ ብሎም የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሪፖርታቸውን ለምክር ቤቱ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እነኚህ ተቋማት ተደጋጋሚ የሕዝብ ቅሬታ እየተነሳባቸው መሆኑ አይዘነጋም፡፡

(ዝርዝር ዘገባው እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል)

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com