ዜና

‹‹ተማሪዎች የገጠማቸው የጤና እክል የምግብ መመረዝ አይደለም››  ም/ል ከንቲባ ታከለ ኡማ

Views: 217

ኢንጅነር ታከለ ኡማ ፍሬህይወት ቁጥር አንድ የአፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት በትላንትናው ዕለት የጤና እክል የገጠማቸውን ተማሪዎችንና በአጠቃላይ የመማር ማስተማር ሂደቱን ጎብኝተዋል፡፡

ምክትል ከንቲባው ተማሪዎች የገጠማቸው የጤና እክል ከምግብ መመረዝ ጋር ግንኙነት እንደሌለውና የሆስፒታል ምርመራ ውጤቱም የምግብ መመረዝ እንዳልሆነ እና ተማሪዎቹም በመልካም ጤንነት  ላይ እንደሚገኙ አይቻለሁ ብለዋል፡፡

በትላንትናው ዕለት በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ተማሪዎቹ በምግብ ተመርዘዋል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ስህተት እንደሆነም አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

በ207 ተማሪዎች ላይ ህክምና ተደርጎ የምግብ መመረዝ እንዳልሆነ ታውቋል ሲል ነው የገለጸው፡፡

የምገባ ፕሮግራሙ በሕግ ደረጃ በከተማችን ምክር ቤት ዓዋጅ ሆኖ ጸድቆ ተቋማዊ በሆነ መልኩ የምገባ መርሃ-ግብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡

በጉብኝታቸው ወቅት የተማሪዎቹን የመመገቢያ ክፍልን ጨምሮ የመማሪያ ክፍሎችን፣ ማብሰያ ቦታዎችን እና የእጅ መታጠቢያ ሥፍራዎችን ለመመልከት ችለዋል፡፡

ኢትዮ-ኦንላይን ዛሬ ህዳር 18 ቀን 2012 በፍሬህይወት ትምህርት ቤት በመገኘት ባደረገው ምልከታ መሠረት ተማሪዎች በመደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ እንዳሉና የጤና እክል የገጠማቸው ተማሪዎችም በትምህርት ገበታቸው እንደሚገኙ ከትምህርት ቤቱ ማኅበረሰብ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ተማሪዎቹን ስለሚገኙበት ኹኔታ ለመጠየቅ የሞከርነው ሙከራ በትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርና በአንድ አንድ መምህራን ፍቃደኛ አለመሆን የተነሳ ለጊዜው ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com