ዜና

ገርጂ አካባቢ የመኪና ሞተር ሳያጠፋ የወረደው ሰው ዓይኑ እያየ መኪናው ተሰረቀ

Views: 273

በአዲስ አበባ ከተማ ገርጂ በሚባለው አካባቢ፣ የመኪናቸውን ሞተር ሳያጠፉ ለአንድ አፍታ ከጋቢና የወረዱ ግለሰብ፣ ዘወር ባሉበት ቅጽበት መኪናቸው ተሰርቋል፡፡

ግለሰቡ የመኪናቸውን ሞተር ሳያጠፉ ለአንዲት ቅጽበት ዘወር ባሉበት ወቅት፣ ኹኔታውን ሲከታተል የነበረ ተጠርጣሪ መኪናውን አስነስቶ ሊያመልጥ መቻሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ግለሰቡ በወቅቱ ላንድክሩዘር መኪናቸውን ከመንገድ ዳር አቁመው ስልክ ለማውራት በወረዱበት ወቅት ነው ተጠርጣሪው ግለሰብ የመኪናው ሞተር እንዳልጠፋ አይቶ በፍጥነት ገብቶ መኪናውን ይዞ ያመለጠው ተብሏል፡፡

መኪናው በጠራራ ጸሐይ ዓይኑ እያየ የተሰረቀበት ግለሰብ “ሌባ…ሌባ” በማለት እየሮጠ መኪናውን በሚከተልበት ወቅት፣ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ሞባይሉን የተነጠቀ መስሏቸው የሚሮጥ ሰው ሲፈልጉ እንደነበር የዓይን እማኞች ለዘጋቢያችን ገልጸዋል፡፡

በዚህ አጋጣሚ በመዲናችን የመኪና ሥርቆት ዓይነቱን እየቀያየር ስለመጣ አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com