ዜና

ተማሪዎች በድንገተኛ ህመም ተጎድተው ሆስፒታል ገቡ

Views: 178

በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ተስፋ ኮከብ ትምህርት ቤት ውስጥ እና እዛው አካባቢ በሚገኝ ፍሬህይወት ቁጥር አንድ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ባጋጠመ ድንገተኛ ህመም 186 ተማሪዎች ሆስፒታል መግባታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የምግብ መመረዝ መሆኑን የትምህርት ቤቱ ሠራተኞች ለኢትዮ-ኦንላይን ጠቁመዋል፡፡

በአዲስ አበባ 186 ተማሪዎች የጤና እክል ገጥሟቸው ሆስፒታል መግባታቸውን የከተማዋ ጤና ቢሮም አስታውቋል።

ጉዳዩ ከምግብ መመረዝ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ሲገለፅ ቢሰማም፣ እስካሁን ትክክለኛ መንስዔው የምርመራ ውጤት አለመውጣቱን የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ተናግረዋል፡፡

የጤና እክሉ ተማሪዎች ቁርስ ከተመገቡ በኋላ መከሰቱን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ቁርስ ያልበሉትም የጤና መታወክ ገጥሟቸው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ገልፀዋል፡፡

ሁሉም ተማሪዎች ታክመው ወደ ትምህርታቸው ተመልሰዋልም ብለዋል፤ ችግሩ ያጋጠመው በልደታ ክፍለ ከተማ ፍሬህይወት ቁጥር 1 አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው፡፡

ትምህርት ቤቱ መንግሥት የጀመረው የምገባ መርሃ ግብር ከሚተገበርባቸው መካከል አንዱ ነው፡፡

ከተማሪዎች በተጨማሪ ችግሩ የገጠማቸው መምህራን እንደነበሩም ተሰምቷል፤ ከዚህ ቀደምም ቁጥሩ በዚህ ልክ ባይሆንም የምግብ መመረዝ ችግር በትምህርት ቤቶች መግጠሙን ጠቅሶ አሐዱ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com