ዜና

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፌደራል ፖሊስ ተይዘው የነበሩ ተማሪዎች ምሽት ላይ ተለቀቁ

Views: 149

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ (ዋናው ጊቢ)፣ ትላንት ኅዳር 15 ቀን 2012 ዓ.ም በፌዴራል ፖሊስ በመኪና ተጭነው የተወሰዱ ተማሪዎች፣ ማምሻውን ወደ ጊቢው በሠላም መመለሳቸውን ተማሪዎች ለኢትዮ-ኦንላይን ገለጹ፡፡

‹‹በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉ ተማሪዎች ይፈቱልን›› በማለት ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የወጡ ተማሪዎችን ትላንት የፌዴራል ፖሊስ ለውይይት እፈልጋችኋለሁ በማለት ከግቢው ውስጥ በመኪና ጭኖ ይዟቸው ከወጣ በኋላ፣ አመሻሹ ላይ ተማሪዎችን እንደለቀቃቸውና ወደ ግቢ በሠላም እንደተመለሱ የስድስት ኪሎ ካምፓስ የኢትዮ ኦንላይን የዜና ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በዛሬው ዕለት የተለመደው ሠላማዊ የመማር-ማስተማር ሂደት እንደቀጠለ እና ተማሪዎችም በትምህርት ገበታቸው ላይ እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

‹‹ሠላም ሲታወክ ቀድሞ የሚጎዳን እኛን ተማሪዎችን ነው፤ እኛ ሠላማችንን በማስጠበቅ ትምህርታችን ላይ ትኩረት በማድረግ ተቸግረው እያስተማሩን ያሉትን ወላጆቻችንን እና ሀገራችንን የምንጠቅምበት ሰዓት ነው እንጂ፤ የምንሞትበት፣ የምንታሰርበትና ግጭት የምንፈጥርበት ወቅት አይደለም›› ሲሉ ተማሪዎቹ ለኢትዮ ኦንላይን ዘጋቢ አብራርተዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com