ዜና

የተባበሩት የአማራ በጎ አድራጎት ማኅበር ሊመሠረት ነው

Views: 198

በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ኹኔታዎች ላይ እየተገፉ ያሉ የአማራ ተወላጆችን ችግር የሚቀርፍ ‹‹የተባበሩት የአማራ በጎ አድራጎት ማኅበር›› ሊመሠረት በሂደት ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ማኅበሩ በልዩ-ልዩ ምክንያቶች ችግር ለሚደርስባቸው የአማራ ተወላጆች ፈጥኖ ምላሽ የሚሰጥ እና ድጋፍ ይሚያደርግ መሆኑን አደራጅ ኮሚቴው ዛሬ በአዲስ አበባ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

የአማራ በጎ አድራጎት ማኅበር የምሠረታ ጉባዔ ሕዳር 21 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ አደራጅ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

በማኅበሩ ሰውን ለመርዳት ፍላጎት ያለው አካል ሁሉ አባል መሆን እና በቻለው አቅም ድጋፍ ማድረግ እንደሚችል ኮሚቴው ጥሪ አስተላልፏል።

አደራጅ ኮሚቴው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝምና ሰብዓዊ መብቶች መምህር የሆኑት ዶክተር ሲሳይ መንግስቴን ጨምሮ፣ የተለያዩ የአማራ ተወላጆችን ያቀፈ ነው ተብሏል።

ማኅበሩ በተለይም ከአማራ ክልል ውጭ ለሚኖሩ የአማራው ሕዝብ ተወላጆች ከለላ እንደሚሆን ይጠበቃል።

በሀገር ውስጥ እና በውጭ አገራት ከሚገኙ አቻ ማኅበራትና ተቋማት ጋርም ለተመሳሳይ ዓላማ በትብብር እንደሚሠራ ተጠቁሟል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com