በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የመገበያያ ማዕከል ሊገነባ ነው

Views: 71

በመዲናችን አዲስ አበባ የዲጅታል ኤሌክትሮኒክስ የግብይት ማዕከል ግንባታን ከአሊባባ ግሩፕ ጋር ለማድረግ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ፡፡

አሊባባ በኢትዮጵያ የሚከፍተው ይህ ዓለም አቀፍ ኤሌክትሮኒክ መገበያያ በውስጡ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት እና የዲጂታል ስልጠና ማዕከልን ያካተተ ነው።

ይህ የግብይት ፕላትፎርም የሀገሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ዘመናዊ ከማድረጉ በተጨማሪ፣ የግብይት ሥርዓቱን የሚደግፍ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

የአሊባባ ግሩፕ መስራች የሆኑት ጃክ ማ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ለጀመረችው የዲጅታል ኢኮኖሚ ጅማሮ እና ሁሉን አቀፍ ለውጥ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት በቀጣይ ሀገሪቱ የጀመረቻቸውን የልማት ሥራዎች በሙሉ በቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ ኩባንያቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

ስምምነቱንም የሳይንስና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ እና የአሊባባ ግሩፕ የቦርድ ሊቀመንበር ተፈራርመዋል፡፡

የአሊባባ ኩባንያ መስራችና ሊቀመንበር የሆኑት ጃክ ማ ትላንት ኅዳር 14 ቀን 2012 ዓ.ም ምሽት ላይ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ እንደገቡ ይታወሳል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com