ዜና

ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ሕጋዊ ሊሆኑ ነው

Views: 465
  • ቄሮ፣ ፋኖ፣ ዘርማ እና ኤጄቶ ሕጋዊ ማዕቀፍ ውስጥ መግባት አለባቸው ተብሏል

በተለያዩ ክልሎች ያሉ ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ሕጋዊ ሊሆኑ እንደሚገባ የሠላም ሚንስቴር አስታወቀ፡፡ በኦሮሚያ ክልል- ቄሮ፣ በአማራ ክልል- ፋኖ፣ በደቡብ ክልል- ዘርማ እና ኢጄቶ እና በሌሎች ክልሎች ያሉ አደረጃጀቶች ሁሉ ወደ ሕጋዊ ማዕቀፍ ሊገቡ ግድ ይላል ብሏል፡፡

እነዚህ አደረጃጀቶችን በአስቸኳይ ወደ ሕጋዊ አደረጃጀት ለማስገባት ደግሞ መንግሥት አቅጣጫማስቀመጡን ነው የሠላም ሚኒስቴር ለኢትዮ-ኦንላይን የገለጸው፡፡

እነዚህ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አደረጃጀቶች በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ተጠያቂነት ባለው አደረጃጀት መመለስ ካልተቻለ፣ የሕግ የበላይነትን ማስከበር አይቻልም ሲሉ የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ጀማል ለኢትዮ-ኦንላይን ተናግረዋል፡፡

በሀገር ላይ እየደረሱ ያሉ ጥፋቶች ቀላል አይለም ያሉት የህዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተሩ፤ እነዚህን ማረምና ማስተካከል ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

ይህም የሆነው  ይላሉ አቶ ደረጄ፤ መደበኛ ያልሆኑ አደረጃጀቶች መደበኛ የሆነውን አደረጃጀት ተግባር እየቀሙ መሆኑን ተከትሎ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም፣ እነዚህ አደራጀቶች ቢፈልጉ በፖለቲካው መስክ፣ ቢፈልጉ ደግሞ በሲቪክ ማህበራት ውስጥ በመካከት ወደ ሕጋዊ አደራጀጀት መግባት ይችላሉ ሲሉ አቶ ደረጄ  ጠቁመዋል፡፡

ለኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ተጠሪ አካል መኖሩ አስፋጊ ነው ያሉን አቶ ደረጄ

እንደ ፍላጎታቸው የመደራጅት መብታቸውን ተጠቅመው መደራጀት ይችላሉ ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በሕጋዊ መንገድ ሲደራጁ  በእድሜ ብቻ እንደማይገደቡም አቶ ደረጄ ገልጸዋል፡፡

በሀገራችን በተለያዩ ክልልሎች በኢመደበኛ አደረጃጀት ውስጥ ያሉ እና  ለውጡ እንዲሰምር የራሳቸውን አሻራ ከጣሉት መካከል ከኦሮሚያ ክልል ‹‹ቄሮ›› ከአማራ ክልል ‹‹ፋኖ›› ከደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች  ደግሞ ‹‹ዘርማ›› እና የሲዳማው ‹‹ኤጄቶ›› ቁልፍ ሚና መጫወታቸው ተነግሯል፡፡

ይሁን እንጂ፣ አነዚህ ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች  ሕጋዊ ባለመሆናቸው የተለያዩ ጥቃቶች ሲፈጸሙ ተጠያቂ እንዳይሆኑ ካደረጋቸው ምክንያቶች በመደበኛ አደረጃጀቶች ውስጥ አለመካከታቸው እንደሆነ  ይጠቀሳል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com