ዜና

ስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የሞከሩ ተማሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

Views: 173

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ (ዋናው ጊቢ) ወደ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያመራ የነበረ የተማሪዎች እንቅስቃሴ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡

ሠልፉ ተካሂዶ ቢሆን በፍጥነት ወደ ግርግርና ግጭት ሊያመራ ይችል እንደነበር መረጃ የነበራቸው የጊቢው ፖሊሶች ለፌዴራል ፖሊስ ማሳወቃቸውን ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ሁለተኛው በር አቅራቢያ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ተማሪዎች ባሉበት እንዲቀመጡ ተደርገው ከፌዴራል ፖሊስ ጋር እየተወያዩ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት (7፡10) በመኪና ተጭነው ከዩኒቨርሲቲው በመውጣት ላይ ናቸው፡፡
(ዝርዝር ዘገባውን ትንሽ ቆየት ብሎ እናቀርባለን)

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com